You are currently viewing በአሸባሪው የትግራይ ወራሪ በሰሜን ሸዋ ዞን  ያወደማቸውን 10 የህክምና ተቋም ግበአቶች መልሶ ለማቋቋም የሲዳማ ክልል ሙሉ ሀላፊነት መውሰዱን አሳወቀ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ  ታህሳስ 2…

በአሸባሪው የትግራይ ወራሪ በሰሜን ሸዋ ዞን ያወደማቸውን 10 የህክምና ተቋም ግበአቶች መልሶ ለማቋቋም የሲዳማ ክልል ሙሉ ሀላፊነት መውሰዱን አሳወቀ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ታህሳስ 2…

በአሸባሪው የትግራይ ወራሪ በሰሜን ሸዋ ዞን ያወደማቸውን 10 የህክምና ተቋም ግበአቶች መልሶ ለማቋቋም የሲዳማ ክልል ሙሉ ሀላፊነት መውሰዱን አሳወቀ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ታህሳስ 20 ቀን 2014 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ የቢሮ ማኔጅመት አባላት፥ የክልሉ የግል ጤና ተቋምናየማህበረሰብ ተወካይ የህክምና ግበአቶችንና ሰበአዊ ድጋፍ በመያዝ በጦርነቱ የተጎዱ የዞኑ የህክምና አገልግሉት መስጫ ተቋማትን ተዘዋውረው የጉዳታቸውን መጠን ለመለየት በሰሜን ሸዋ ተገኝተው ከዞኑ ጤና መምሪያ ጋር የመረጃ ልውውጥ አድርገዋል። በአዲሱ የሲዳማ ክልል የጤና ቢሮ የተመራው ቡድን በዞኑ በወራሪው የትግራይ ኃይል ከወደሙት ውስጥ 10ን የህክምና ጤና ተቋማት ወደነበሩበት አገልግሎት ስራቸው እንዲመለሱ ለማድረግ 3ሚሊየን የማገመት የመጀመሪያ ዙርየሰበአዊ ድጋፍና የህክምና ግበአቶችን በመያዝ ወደተጎዱ አካባቢዎች አንፆኪያ ገምዛና ኢፍራታና ግድም አቅንተዋል። የሲዳማ ቢሔራዊ ክልላዊ መንግስት ጤና ቢሮ ሀላፊ ዶክተር ሰላማዊት መንገሻ እንደገለፁት የፌደራል ጤና ጥበቃ ሚኒስተር ባደረገው ጥሪ መሰረት የዞናችን ጤና ቢሮ የማኔጅመት አባላት የህብረተሰብ ተወካዮች በአማራ ክልል በትግራይ ወራሪ ኃይል ከወደሙት የህክምና ተቋማት ውስጥ በሰሜን ሸዋ ዞን የሚገኙትን 10የህክምና ተቋሞችን ወደነበረ አገልግሎታቸው እንዲመለሱ ድጋፍ ለመድረግ ስራ መጀመራቸውን ተናግረዋል። የአማራ ክልል ጤና ቢሮ ምክትል ኃላፊ ጋሹ ክንዱ አንደ ገለፁት የሲዳማ ክልል ጤና ቢሮ የአማራ ክልል በወራሪ የትግራይ ኃይል ያደረሰውን ችግር ለመጋራት የወሰደውን ኃላፊነት በተመለከተ በዚህ ክፉቀን በጎናችን በመቆም ሊሰሩት ያቀዱት በጉ ተግባር ወደፊት በታሪክ ተሰንዶ የሚቀመጥ አሻራነው በማለት የገለፁ ሲሆን በክልሉ ጤና ቢሮ ስም ምስጋና አቅርበዋል።

Source: Link to the Post

Leave a Reply