You are currently viewing “በአሸናፊ አካሉ ላይ እገታ የፈፀመው የይልቃል ከፋለ መንግስት!” ክርስቲያን ታደለ  አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ …     ጥር 15 ቀን 2015 ዓ/ም           አዲስ አበባ ሸዋ የም…

“በአሸናፊ አካሉ ላይ እገታ የፈፀመው የይልቃል ከፋለ መንግስት!” ክርስቲያን ታደለ አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ … ጥር 15 ቀን 2015 ዓ/ም አዲስ አበባ ሸዋ የም…

“በአሸናፊ አካሉ ላይ እገታ የፈፀመው የይልቃል ከፋለ መንግስት!” ክርስቲያን ታደለ አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ … ጥር 15 ቀን 2015 ዓ/ም አዲስ አበባ ሸዋ የምዕራብ ጎጃም ዞን የአብን ማስተባበሪያ ጽ/ቤት ምክትል ሰብሳቢ የሆነው ወንድማችን አሸናፊ አካሉ ከመኖሪያ ቤቱ ታፍኖ ከታገተ እነሆ ከሳምንት በላይ ሆኖታል። እስከዛሬ ድረስም ፍርድ ቤት አልቀረበም። በይልቃል ከፋለ የሚመራው የክልሉ መንግስት አሸናፊን ዓባይ ማዶ በሚገኝ የልዩ ኃይል ካምፕ አግቶ ማስቀመጡን ያመነው እንኳን ከስንት ጉትጎታና ጩኸት በኋላ በቅርቡ ነው። የክልሉ መንግስት የፀጥታ አመራሮች የመንግስት ደመወዝ የሚከፈላቸው አጋቾች ሆነው የሚቀጥሉት እከመቼ ድረስ ነው? ንጹኃን ዜጎችን እያፈኑ ያለፍረድ የሚያግቱበት የሥልጣን ምንጫቸውስ ምንድን ነው? ዛሬ ንጹኃን ዜጎችን አፍኖ ማገትን እንደልከኛ ተግባር የሚቆጥር የነውር ቡድን ነገ የመንግስት የሥራ ኃላፊዎችን አፍኖ ላለማገቱስ ምን መተማመኛ ይኖራል? ስለአፈናው አቤቱታ የቀረበላቸው የምርጫ ቦርድና የሰብአዊ መብቶች ኮሚሽንስ ዝምታቸው እስከመቼ ነው?

Source: Link to the Post

Leave a Reply