በአቃስታ ግንባር የተሰው ጀግኖች ሥርዓተ ቀብር ተፈጸመ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ህዳር 30 ቀን 2014 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ በደብረ ማርቆስ ከተማ ግንባር ከተሰለፉ የፀጥ…

በአቃስታ ግንባር የተሰው ጀግኖች ሥርዓተ ቀብር ተፈጸመ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ህዳር 30 ቀን 2014 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ በደብረ ማርቆስ ከተማ ግንባር ከተሰለፉ የፀጥታ አባላት መካከል ህዳር 8 በአቃስታ ግንባር አኩሪ ጀብድ ፈፅመው የተሰዉ ጀግኖች በከተማዋ ንጉስ ተክለ-ሃይማኖት አደባባይ የጀግና አቀባበል ተደርጎላቸው በክብር ሥርዓተ ቀብራቸው ተፈጽሟል፡፡ “እነኝህ ጀግኖች አማራ ሲዋረድና ኢትዮጵያን ስትፈርስ ቁመን አናይም በማለት በግንባር በመሰለፍ በርካታ የጠላትን ሃይል እንደ ቅጠል በማርገፍ የተሰው ጀግኖች ሲሆኑ ታሪክም በክብር መዝገብ አስቀምጦ ሲዘክራቸው ይኖራል።” እንደሚኖር የደብረ ማርቆስ ኮሚኒኬሽ ቢሮ አስታውቋል፡፡ “ይህን አረመኔ ቡድን ለመደምሰስ ዛሬ በክብር እንደተቀበሩት ጀግኖቸ ሁሉ መላው አማራ እንዲሁም የኢትዮጵያ ህዝብ መስዋትነት በመክፈልም ቢሆን እስከመጨረሻው ሊፋለማቸውና ሊጠፋቸው ይገባል” ያሉት ደግሞ የተሰው ጀግኖች ቤተሰብ ናቸው። የሰማዕታት ቤተሰቦች የጀግኖቻችን ደም ለአገር ክብር የተከፈለ መስዋትነት ስለሆነ ኩራት ይሰማናል ብለዋል፤ በቀጣይም የተሰዉለትን አላማ ለማሳካትና ጠላትን ለማፅዳት እንፋለማለን ብለዋል፡፡ በቀብር ሥነ-ሥርዓቱ ላይ የተገኙ ወጣቶች እንደተናገሩት ጀግኖች መስዕዋት የሆኑለትን የጀግንነት ተጋድሎ ዳር ለማድረስና ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ጠላትን ለመደምሰስና የአማራን ብሎም የኢትዮጵያን ታሪክ ከፍ ለማድረግ የአገር መከላከያ ሰራዊትን፣ የአማራ ልዩ-ሃይልን እንዲሁም ሚሊሻና ፋኖን በመቀላቀል የህይወት መስዋትነት ለመክፈል ዝግጁ ነን ብለዋል፡፡ በቀብር ሥነ ሥርዓቱ ላይም የከተማዋ ነዋሪዎች፣ የመንግስት የሥራ ሃላፊዎች፣ የፀጥታ አካላትና የሃይማት አባቶች መገኘታቸውን ከደብረ ማርቆስ ከተማ ኮሙኒኬሽን የማህበራዊ ትስስር ገጽ የተገኘው መረጃ አመልክቷል።

Source: Link to the Post

Leave a Reply