በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ወድቆ የተገኘ ቦምብ ፈንድቶ የአንድ ህጻን ህይወት አለፈ

በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ወድቆ የተገኘ ቦምብ ፈንድቶ የአንድ ህጻን ህይወት አለፈ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 20፣2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ወረዳ 8 ልዩ ቦታው ደራርቱ ቱሉ መሰናዶ ትምህርት ቤት ጀርባ ዛሬ ታህሳስ 20 ቀን 2013 ዓ.ም ከቀኑ በግምት 8 ሰዓት ተኩል ሁለት ህፃናት ወድቆ ያገኙትን ቦንብ ሲነካኩ ፈንድቶ የአምስት ዓመት እድሜ ያለው ህፃን ፀጋዬ ተክለማርያም ህይወቱ ሲያልፍ የስምንት ዓመቱ ህፃን ግዛው አንተን አየሁ በእግሩ ላይ ጉዳት ደርሶበት ህክምና እንደተደረገለት ከአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።
ፖሊስ ኮሚሽኑ አያይዞም ተጨማሪ መረጃ እንደደረሰው ዝርዝሩን እንደሚያስታውቅ ገልጿል።
ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል www.youtube.com/fanatelevision ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

The post በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ወድቆ የተገኘ ቦምብ ፈንድቶ የአንድ ህጻን ህይወት አለፈ appeared first on Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C.

Source: Link to the Post

Leave a Reply