በአቃቂ ክ/ከተማ በደረሰ የመኪና አደጋ የሰው ህይወቱ ማለን ሰምተናል። በአዲስ አበባ ከተማ አቃቂ ክ/ከተማ ወረዳ 2 ልዩ ቦታው ቱሉዲምቱ ቀለበት መንገድ ላይ ሰሌዳ ቁ ኮድ 3-75318 የሆነ…

በአቃቂ ክ/ከተማ በደረሰ የመኪና አደጋ የሰው ህይወቱ ማለን ሰምተናል።

በአዲስ አበባ ከተማ አቃቂ ክ/ከተማ ወረዳ 2 ልዩ ቦታው ቱሉዲምቱ ቀለበት መንገድ ላይ ሰሌዳ ቁ ኮድ 3-75318 የሆነ አንድ ሲኖትራክ እና የሰሌዳ ቁ 3-75549 ሚኒባስ ተጋጭተው በግጭቱ የሚኒባስ አሽከርካሪው ህይወት ሊያልፍ ችሏል።

የአሽከርካሪውን አስክሬን በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የእሳት እና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን ሠራተኞች አማካኝነት ሚኒባሱን በመፈልቀቅ አውጥተው ለመርማሪ ፖሊስ አስረክበዋል።

በሳምንቱ ክስተቶች የተሽከርካሪ አደጋ እየበዛ በመሆኑ ህብረተሰቡ በሚያሽከረክርበት ጊዜ በራሱ ብሎም በሌሎች ላይ የህይወት መጥፋት እና ንብረት መውደምን እንዳያስከትል በጥንቃቄ እንዲያሽከረክር የበኩሉን ድርሻ እንዲወጣ ኮሚሽኑ መልክቱን አስተላልፎአል።

ባሳለፍነው ሳምንት ብቻ 3 የተሽከርካሪ አደጋ ክስተቶችን ያስተናገድን ሲሆን በዚህም የ10 ሰዎች ህይወት ሲጠፋ በ6 ሰዎች ላይም ከባድ ጉዳት መድረሱንም የኮሚሽኑ ህዝብ ግንኙነት በማህበራዊ ትስስር ገጹ አስታውቋል።

ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያውያን
መጋቢት 09 ቀን 2014 ዓ.ም

Source: Link to the Post

Leave a Reply