You are currently viewing በአቢደንጎሮ ወረዳ የሚገኙ ከ300 ያላነሱ የ12ኛ ክፍል ተማሪዎች ለፈተና ወደ ሻምቡ አጅቦ የሚወስዳቸው የመንግስት አካል እንዳላገኙ ተናገሩ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ    ታህሳስ 15 ቀን…

በአቢደንጎሮ ወረዳ የሚገኙ ከ300 ያላነሱ የ12ኛ ክፍል ተማሪዎች ለፈተና ወደ ሻምቡ አጅቦ የሚወስዳቸው የመንግስት አካል እንዳላገኙ ተናገሩ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ታህሳስ 15 ቀን…

በአቢደንጎሮ ወረዳ የሚገኙ ከ300 ያላነሱ የ12ኛ ክፍል ተማሪዎች ለፈተና ወደ ሻምቡ አጅቦ የሚወስዳቸው የመንግስት አካል እንዳላገኙ ተናገሩ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ታህሳስ 15 ቀን 2015 ዓ/ም አዲስ አበባ ሸዋ በሆሮ ጉድሩ ወለጋ ዞን በአቢደንጎሮ ወረዳ ቱሉዋዩ እና ቱሉጋናን ጨምሮ ከ300 ያላነሱ የአማራ ተወላጅ የሆኑ የ12ኛ ክፍል ተማሪዎች መንግስት የአካባቢውን ሰላም እና ደህንነት ማስከበር ባለመቻሉ በፈተና ላይ ላይቀመጡ እንደሚችሉ አስታውቀዋል። የ12ኛ ክፍል ተማሪዎች በአካባቢው ባለው የጸጥታ ችግር ምክንያት እንዲራዘም ለተደረገው ሀገር አቀፍ ፈተና በመዘጋጀት ከታህሳስ 14/2015 ጀምሮ ፈተና ወደሚሰጥበት ሻምቡ እንዲገኙ ተነግሯቸው ነበር። ፈተናው የሚሰጠውም ታህሳስ 18/2015 ሻምቡ ላይ ስለመሆኑ ተገልጧል። ይህን መሰረት በማድረግ ታህሳስ 14/2015 ወደ ቱሉዋዩ ት/ቤት በማቅናት የእጀባ ድጋፍ እንዲደረግላቸው የአማራ ተወላጅ የሆኑ ተማሪዎች ጠይቀዋል። ችግሩ በት/ቤቱ እንደማይፈታ በመግለጽ ወደ ወረዳ ሄደው እንዲጠይቁም ተደርጓል። ይሁን እንጅ የአቢደንጎሮ ወረዳ መስተዳድርም የኦሮሞ ተወላጅ የሆኑ ተማሪዎች በግላቸው በሄዱበት ሁኔታ ለእናንተ መኪና እና አጃቢ አናዘጋጅም በማለቱ ታህሳስ 18 ይሰጣል የተባለው ፈተና ሊያልፈን ነው ሲሉ ቅሬታ አቅርበዋል። የኦሮሞ ተወላጅ የሆኑ ሰዎች ከቦታ ቦታ ቢንቀሳቀሱ የሚነካቸው የለም፤ ነገር ግን የአማራ ልጆች ከከተማ እንኳ ሲወጡ እየታገቱ ይገደላሉ ይላሉ ተማሪዎቹ። እንደአብነትም በ2014 ክብረቱ የተባለ ለ20 ዓመታት በአዕምሮ ህመም እየተሰቃዬ የሚኖርን ሰው፣ አማራ በመሆኑ ብቻ እሁዲት በተባለ አካባቢ መንገድ ላይ በመገኘቱ በጽንፈኛ የታጠቁ ኦነጋዊያን ተገድሏል። አሁንም የአማራ ተወላጅ የሆኑ የ12ኛ ክፍል ተፈታኝ ተማሪዎች ታህሳስ 18/2015 ይሰጣል የተባለውን ፈተና የኦሮሞ ልጆች ብቻ ከሚፈተኑ እነሱም በሻምቡ በመገኘት ይፈተኑ ዘንድ የሚመለከተው አካል አስቸኳይ መፍትሄ እንዲሰጣቸው ጠይቀዋል።

Source: Link to the Post

Leave a Reply