You are currently viewing በአቢ ደንጎሮ፣ በጃርዴጋ ጃርቴ እና በጊዳ አያና ወረዳ የታሰሩ አማራዎች ፍትህ መነፈጋቸው ተነገረ፤ በእስር ቤት በኦነግ አባላት እንዲሰቃዩ እየተደረገ መሆኑ ተገልጧል። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አ…

በአቢ ደንጎሮ፣ በጃርዴጋ ጃርቴ እና በጊዳ አያና ወረዳ የታሰሩ አማራዎች ፍትህ መነፈጋቸው ተነገረ፤ በእስር ቤት በኦነግ አባላት እንዲሰቃዩ እየተደረገ መሆኑ ተገልጧል። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አ…

በአቢ ደንጎሮ፣ በጃርዴጋ ጃርቴ እና በጊዳ አያና ወረዳ የታሰሩ አማራዎች ፍትህ መነፈጋቸው ተነገረ፤ በእስር ቤት በኦነግ አባላት እንዲሰቃዩ እየተደረገ መሆኑ ተገልጧል። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ የካቲት 22 ቀን 2014 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ በሆሮ ጉድሩ ዞን አቢ ደንጎሮ ወረዳ ከዛሬ አንድ ዓመት በፊት በአማራዊ ማንነታቸው የታሰሩት:_ 1) አቶ የሱፍ ይርጋ እና 2) አቶ መሀመድ ያሲን ከታሰሩ አንድ ዓመት አልፏቸዋል። ቤተሰብ በነጻነት ውሃ፣ምግብ እና ሌሎች ግብአቶችን ለማቅረብ እየተቸገሩ ነው። በመንገድ ላይ በርካታ የመንግስት አካላት የሚደግፉት አራጁ የኦነግ ሸኔ ቡድን መታወቂያ እያዬ አማራን ስለሚዘርፍ፣ ስለሚያግትና ስለሚጨፈጭፍ ክፉኛ ተቸግረዋል። ከወራት በፊት በአቢደንጎሮ ታስረው የሚገኙ እና ስንቅ የማይደርሳቸው አማራዎች:_ 1) ደምረው አንዳርጌ፣ 2) ሞላ አንዳርጌ፣ 3) ጌታቸው ብርሌው፣ 4) ፀጋዬ ሞላ፣ 5) ደመቀ ሞላ እና 6) ካሳዬ አይነታው፣ በአቢ ደንጎሮ ወረዳ ከእስር እና ከጥቃት የሸሹ አማራዎች በጫካ ገብተው እየታደኑ ይገኛሉ። በተመሳሳይ በጃርዴጋ ጃርቴ ወረዳ ጃርዴጋ እና በደርጌ ኮቲቻ በርካታ ህጻናትና ሚሊሾች በአማራነታቸው ታስረው ይገኛሉ። ከዚህ በተጨማሪ በምስራቅ ወለጋ ዞን በጊዳ አያና ወረዳ ከመንደር 10 በወርሃ የካቲት 2013 ታስረው ወደ ነቀምት የተወሰዱ 31 ባለሀብቶችን ጨምሮ አያሌ አማራዎች ዛሬም በግፍ እስር ላይ ናቸው። ቢሮ ላይ ያለው ኦነግ ጫካ ካለው ጋር በመመሳጠር የዘር ማጥፋት ወንጀልን በማስቀጠል ላይ ይገኛል የሚሉት በርካቶች ናቸው።

Source: Link to the Post

Leave a Reply