
አዲስ አበባ ፣ ታህሳስ 17 ፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በኦሮሚያ ክልል ርእሰ መስተዳድር አቶ ሽመልስ አብዲሳ የተመራ ልኡክ በኦሮሚያ ክልል በፊንፊኔ ዙሪያ ልዩ ዞን ባራክ ወረዳ ቡራ እና አለልቱ ጨፌ ቀበሌዎች በመስኖ የለማ የስንዴ ማሳን ጎብኝቷል።
በተጨማሪም በርእሰ መስተዳድር አቶ ሽመልስ የተመራው ልኡክ በዞኑ በህብረተሰቡ ተሳትፎ በመገንባት ላይ ያለ የባራክ 1ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ጎብኝቷል።
በህብረተሰቡ ተሳትፎ እየተገባ ያለው ትምህርት ቤት እስከ ቀጣዩ ሰኔ ወር ድረስ ግንባታው ተጠናቆ ከ3 ሺህ 600 በላይ ተማሪዎቸን ይቀበላል ተብሎ እንደሚጠበቅም ተገልጿል።
በጉብኝቱ ወቅትም የቡራ አለልቱ እና ጨፌ ኩሎ ቀበሌ አርሶ አደሮች ለርእሰ መስተዳድር ሽመልስ አብዲሳ አጋርነታቸውን በመግለፅ የፈረስ፣ ጦር እና ጋሻ እንዲሁም ጋቢ አበርክተውላቸዋል።
ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል www.youtube.com/fanatelevision ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
The post በአቶ ሽመልስ አብዲሳ የተመራ ልኡክ በፊንፊኔ ዙሪያ ልዩ ዞን በመስኖ የለማ የስንዴ ማሳን ጎበኘ appeared first on Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C.
Source: Link to the Post