You are currently viewing በአቶ እስክንድር ነጋ ላይ ስለተፈጸመው ከባድ ድብደባ ጠቅላይ አቃቤ ህግ አስቸኳይ ማብራሪያ እንዲሰጥ ተጠየቀ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ  ጥቅምት 12 ቀን 2014 ዓ. ም         አዲስ…

በአቶ እስክንድር ነጋ ላይ ስለተፈጸመው ከባድ ድብደባ ጠቅላይ አቃቤ ህግ አስቸኳይ ማብራሪያ እንዲሰጥ ተጠየቀ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ጥቅምት 12 ቀን 2014 ዓ. ም አዲስ…

በአቶ እስክንድር ነጋ ላይ ስለተፈጸመው ከባድ ድብደባ ጠቅላይ አቃቤ ህግ አስቸኳይ ማብራሪያ እንዲሰጥ ተጠየቀ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ጥቅምት 12 ቀን 2014 ዓ. ም አዲስ አበባ ሸዋ በግፍ እስር ላይ የሚገኙት የባልደራስ ለእውነተኛ ዴሞክራሲ ፓርቲ (ባልደራስ) ፕሬዚደንት አቶ እስክንድር ነጋ በሚኖሩበት ቂሊንጦ ወህኒ ቤት ውስጥ ጥቅምት 11/2014 ዓ.ም. ንጋት 12፡20 ደቂቃ ላይ ከፍተኛ ድብደባ እንደተፈጸመባቸው ተገልጧል፡፡ ከአቶ እስክንድር ነጋ ጋር አብረው በእስር ላይ ያሉት የፓርቲው የአደረጃጀት ጉዳዮች ኃላፊ አቶ ስንታየሁ ቸኮል ጥቅምት 11 ቀን 2014 ዓ.ም. በነበረው የፍርድ ቤት ቀጠሮ የተገኙ ሲሆን የባልደራስ ፕሬዝዳንት ወህኒ ቤት ውስጥ በተደራጀ የውንብድና ቡድን መደብደባቸውን ተናግረዋል። በዚህም ምክንያትም አቶ እስክንድር ፍርድ ቤት መቅረብ እንዳልቻሉ ገልጸዋል። ከችሎት መልስ የአቶ እስክንድር ጠበቆች፣ ቤተሰቦቻቸው፣ የባልደራስ አመራሮችና አባላት ወደ ቂሊንጦ ወህኒ ቤት ሄደው ለመጠየቅ ቢሞክሩም አቶ እስክንድር ከታሰሩበት ክፍል ወጥተው ማነጋገር አልቻሉም። ሆኖም በተፈጸመባቸው ድብደባ ግንባራቸው፣ ዓይናቸው አካባቢ እና ጉልበታቸው ጉዳት የደረሰባቸው መሆኑን ባልደራስ አረጋግጫለሁ ብሏል። ነገር ግን ለደረሰባቸው ጉዳት የተደረገላቸው ህክምና አለመኖሩን ጠቅሶ በአስቸኳይ ቤተሰቦቻቸው ወደ መረጡት ሆስፒታል ተወስደው እንዲታከሙ እንጠይቃለን ብሏል። ድብደባው በፌዴራል ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ እና መሥሪያ ቤቱን በቀጥታ በሚቆጣጠረው ጠቅላይ ሚንስትር ቢሮ ሊፈጸም እንደቻለ መገመት አስቸጋሪ አይሆንምም ነው ያለው። ይህም የኅሊና እስረኞችን በተለይም የአቶ እስክንድር ነጋን ህይወት ለመቅጠፍ የሕብረተሰቡን አስተሳሰብ ማለማመጃ ምዕራፍ እንደሆነ ይረዳል ያለው ባልደራስ ስለተፈጸመው ከባድ ድብደባ ጠቅላይ አቃቤ ህግ በቀጥታ ለሕዝብ መግለጫ እንዲሰጥ ጠይቋል። ፓርቲው ይህን ያለው አቶ እስክንድር ነጋ ከዚህ በፊት በፌዴራል ፖሊስ ወንጀል ምርመራ ቢሮ፣ በቃሊቲ ወህኒ ቤት እንዲሁም ሰኔ 24 ቀን 2012 ዓ.ም. በወታደር ቁጥጥር ስር በዋሉበት ጊዜ እና ቢሯቸው ውስጥ የደረሱባቸውን በመጠን የተለያዩ ድብደባዎች ሁሉ በማስታወስ እንደሆነ ጠቅሷል። በተያያዘም ጥቅምት 11/2014 ዓ.ም. በእነአቶ እስክንድር ነጋ የፍርድ ሂደት ችሎት ታድመው የነበሩ 42 የፓርቲያችን አባላት ታፍሰው ልደታ ክፍለ ከተማ የፖሊስ መምሪያ ከቆዩ በኋላ አመሻሹ ላይ 5ኛ ፖሊስ ጣቢያ ተወስደው እንዲታሠሩ ተደርገዋል፤ ከታሠሩት ውስጥ 12ቱ ሴቶች መሆናቸውም ተረጋግጧል፡፡ ባልደራስ ለእውነተኛ ዲሞክራሲ ፓርቲ የታሠሩት አባሎቹ ያለ አንዳች ቅድመ ሁኔታ በአስቸኳይ ከእስር እንዲለቀቁም ጠይቋል።

Source: Link to the Post

Leave a Reply