በአንኮበር ወረዳ ጎረጎ ዙሪያ ቀበሌ የደረሰ ከፍተኛ የመሬት መንሸራተት በአርሶ አደሮች ማሳ ላይ ጉዳት አደረሰ፡፡ አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ታህሳስ 30 ቀን 2013 ዓ.ም         አዲስ…

በአንኮበር ወረዳ ጎረጎ ዙሪያ ቀበሌ የደረሰ ከፍተኛ የመሬት መንሸራተት በአርሶ አደሮች ማሳ ላይ ጉዳት አደረሰ፡፡ አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ታህሳስ 30 ቀን 2013 ዓ.ም አዲስ…

በአንኮበር ወረዳ ጎረጎ ዙሪያ ቀበሌ የደረሰ ከፍተኛ የመሬት መንሸራተት በአርሶ አደሮች ማሳ ላይ ጉዳት አደረሰ፡፡ አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ታህሳስ 30 ቀን 2013 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ በአንኮበር ወረዳ ጎረጎ ዙሪያ ቀበሌ በርበሬ ውሃ በተባለው ጎጥ በተከሰተው የመሬት መንሸራተት ከ32 በላይ አርሶ አደሮች የእርሻ መሬት በከፍተኛ ሁኔታ ተጎድቷል፡፡ የጉዳቱን መጠን ለማየትና መፍትሔ ለመስጠት በወረዳው ጤና ጥበቃ ጽ/ቤት ኃላፊና ምክትል አስተዳዳሪ አቶ አዲሱ አስጨናቂ የተመራ የልዑካን ቡድን በቦታው ላይ ታኅሳስ 28/2013 ዓ.ም ተገኝቶ ቅኝትና ውይይት ማድረጉ ተገልጧል፡፡ በውይይቱም አርሶ አደሮቹ በተፈጠረው ነገር ክፉኛ ማዘናቸውን ገልጸው፣ ችግሩ መሬታቸውን ብቻ ሳይሆን ለሕይወታቸውም በሰቀቀን ተኝተን እየተነሳን ሲሆን አንድ ቀን በዚህች ጎጥ አሳዛኝ ክስተት ሳይፈጠር መንግሥት ለጊዜው ልጆቻችንንና ከብቶቻችንን የምናሰፍርበት ቦታ እንዲሰጠን ሲሉ ጠይቀዋል፡፡ የወረዳው ጤና ጥበቃ ጽ/ቤት ኃላፊና ምክትል አስተዳዳሪ አቶ አዲሱ አስጨናቂና ባልደረቦቻቸው በሰጡት ምላሽ ችግሩ በወረዳው አቅም የሚፈታ አይደለም ተጨማሪ ጥናትም ይጠይቃል ብለዋል። አቶ አዲሱ ሲቀጥሉ “በጊዜያዊነት ከቦታው ተነስታችሁ ወደ ሌላ አካባቢ እንድትሰፍሩ ቦታ እናመቻቻለን፤ ቦታውም እስኪመቻች በአፋጣኝ ለቃችሁ በአቅራቢያ ወዳሉ ከተሞች ቤት ተከራይታቸሁ ልጆቻችሁን ከጥፋት ታደጉ፣ ችግሩን በዘላቂነት ለመፍታት ከሚመለከታቸው አካላት ሁሉ ጋር እንነጋገራለን” ስለማለታቸው የዘገበው የወረዳው ኮሙኒኬሽን ነው፡፡

Source: Link to the Post

Leave a Reply