በአንድ ወቅት ከፍተኛ የቦታ ጥበት አጋጥሞት የነበረው የካ ኮተቤ ሆስፒታል ዛሬ አንድም የኮቪድ 19 ታካሚ እንደሌለው አስታወቀ።
ሆስፒታሉ ትላንትና የመጨረሻውን የኮቪድ-19 ታካሚ በሰላም ወደ ቤቱ መሸኘቱን እና ሆስፒታሉ በሁለት አመት ውስጥ ለመጀመሪያ ጊዜ ያለ ኮቪድ19 ታካሚ ውሎ ማደሩን የሆስፒታሉ ስራ አስኪያጁ ዶ/ር ያሬድ አግደው በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ላይ አስፍረዋል።
” በትናንትናው ዕለት የመጨረሻውን ታካሚ ወደ ቤቱ በሰላም ሸኝተናል ” ያሉት ዶ/ር ያሬድ ” በሁለት አመት ውስጥ ለመጀመሪያ ጊዜ ሆስፒታሉ ያለ ኮቪድ 19 ታካሚ ውሎ ማደሩን ገልፀዋል።
” ከዚህ በኋላ ሀገርን በሚጎዳ መልኩ የኮቪድ 19 ማዕበል በሀገራችን በድጋሚ እንዳይከሰት ሁላችንም የድርሻችን መወጣት ይኖርብናል ” ሲሉም መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።
ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያን
ሚያዝያ 28 ቀን 2014 ዓ.ም
Source: Link to the Post