በአንድ ዓመት በአዲስ አበባ ከ6 መቶ 30 ሺ በላይ አሽከርካሪዎች ህግ በመጣስ ለቅጣት ይዳረጋሉ፡፡

የአዲስ አበባ ትራፊክ ማኔጅመንት ኤጀንሲ በመዲናዋ ከደንብና መመሪያ ጥሰት ጋር በተያያዘ ሰፊ ቁጥጥር እያደረገ እንደሚገኝ ገልጿል፡፡በሚደረጉ ቁጥጥሮች በአመት ውስጥ ከ630 ሺ በላይ አሽከርካሪዎች እንደሚቀጡ አዲስ አበባ ትራፊክ ማኔጅመንት ኤጀንሲ ዋና ዳሬክተር አቶ ጂሬኛ ሄርጳ ለአሐዱ ገልጸዋል፡፡

በመዲናዋ ከትራፊክ ፍሰት ጋር ተያይዞ የሚደረሰውን አደጋ ለመቀነስና ህብረተሰቡን ከአደጋ ለመታደግ ዘመናዊ የእግረኛ የትራፊክ መብራቶችን ተግባራዊ ማድረግ አንዱ እንደሆነ ኤጀንሲው ገልጿል፡፡ዋና ዳሬክተሩ ቴክኖሎጂው አዲስ ከመሆኑ ጋር ተያይዞ አጠቃቀም ላይ ክፍተት የነበረ ቢሆንም አሁን ላይ በሚፈለገው መጠን ለውጥ ማምጣቱን አስታውቀዋል፡፡

********************************************************************************

ቀን 08/04/2013

Source: Link to the Post

Leave a Reply