You are currently viewing በአንገር ጉትን ከተማና በዙሪያው በሚገኙት አከባቢዎች የኦነግ ሸኔን በህዝባችን ላይ የሚያደርሰውን የጅምላ ግድያ እና ጭፍጨፋ ለማስቆም የሚያግዝ አምስት እዞችን ፈጥሪያለሁ ሲል ገለፀ። ሰ.አሜ…

በአንገር ጉትን ከተማና በዙሪያው በሚገኙት አከባቢዎች የኦነግ ሸኔን በህዝባችን ላይ የሚያደርሰውን የጅምላ ግድያ እና ጭፍጨፋ ለማስቆም የሚያግዝ አምስት እዞችን ፈጥሪያለሁ ሲል ገለፀ። ሰ.አሜ…

በአንገር ጉትን ከተማና በዙሪያው በሚገኙት አከባቢዎች የኦነግ ሸኔን በህዝባችን ላይ የሚያደርሰውን የጅምላ ግድያ እና ጭፍጨፋ ለማስቆም የሚያግዝ አምስት እዞችን ፈጥሪያለሁ ሲል ገለፀ። ሰ.አሜሪካ:- ሰኔ 19/2014 ዓ.ም አሻራ ሚዲያ በሐገራችን በተፈጠረው ግጭት ሳቢያ በየቀበሌው ከሚኒሻው በተጨማሪ ሶስት ሶስት መቶ ወጣቶች ሰልጥነው አካባቢያቸውን እንድጠብቁ በሚል በተላለፈው የፌዴራል እና የክልሉ መንግስት አዋጅ መሠረት በሁሉም ቀበሌዎች የሠለጠኑ ወጣቶችን ወደአንድ በማምጣት ለመከላከል የሚያግዝ አምስት እዞችን መፈጠራቸውን አጉልዞ ጥያቄ ለህዝባችን ገልጻል። የተፈጠሩት እዞች መካከል፦ 1- የምስራቅ ጉትን እዝ 2- ምዕራብ ጉትን እዝ 3- ሰሜን ጉትን እዝ 4- ደቡብ ጉትን እዝና 5- ማዕከላዊ ጉትን በማለት የተፈጠሩ ሲሆን አንዳዶቹ ወደስራ መግባታቸውን ገልጻል። ወደስራ ከገቡት ውስጥ የምስራቅ ጉትን እዝ በመካከላቸው የነበረውን ልዩነት ወደጎን በመተው በሎሚጫ በኩል እና በጃርቴ ጃርዴጋ በኩል ያለውን የሸኔ እንቅስቃሴ ለመመከት በመንደር 25 (ለጋ ጊምቢ) ቀበሌ ሊቀመንበር የሆኑት አቶ ካሳ ጌታቸውን እና የኦነግ ሸኔ መድኃኒት የሆነው አስር አለቃ መሐመድ ያሲን የተባለው የቀበሌው ሚኒሻ ከእስር ከተፈታ ቡኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ ሁለታቸውን አጉልዞ ጥያቄ በሐገር ሽማግሌዎች፣ በሐይማኖት አባቶች እና ከተለያዩ አከባቢ በተውጣጡ የማህበረሰብ ክፍሎች በተሰበሠቡበት የማይጎረብጥ እርቅ በማድረግ በፊታችን የተጋረጠውን አደጋ በጋራ ለመከላከል ተስማምተዋል። በሽምግልና ስነስርአቱ የሐገር ሽማግሌዎች በሁለታቸው እርቅ የምስራቅ ጉትን ህዝብ እጅጉንም የሚጠቀም በመሆኑ በጋራ ለመቆም ለህብረተሰቡ ሰላም መተኪያ የሌለው ነውና ወታደራዊ ክህሎቱን ለወጣቶች እና ለሁሉም የማህበረሰብ ክፍል በማካፈል አከባቢውን በበላይነት አስር አለቃ መሐመድ ያሲን እንድመራ ውሳኔ ተላልፋል። አስር አለቃ መሐመድ ያሲንም የህዝቡን ውሳኔ ተቀብሎ ለመስራት የሚያስችለውን በጎ ምላሹን ቢገልፅም ወረዳው ለነመሳሪያዬ አስሮኝ ስለነበር እኔን ከስድስት ወር በላይ አስሮ ፈትቶኛል፤ መሳሪያዬን ግን እስካሁን አልሰጠኝም። ስለዚህ አቶ ካሳ ጌታቸው ደግሞ የቀበሌያችን ሊቀመንበር በመሆናቸው መሳሪያዬን ከወረዳው በኩል ያለውን ጨርሰው መሳሪያዬን እንድያስለቅቅልኝ ስል እጠይቃለሁ። ብሏል። አቶ ካሳ ጌታቸውም የመሳሪያውን ጉዳይ ወንጀል ያልሰራና በስራ ላይ እያለህ የተወሰደ በመሆኑ ወረዳው መሳሪያውን ለቀበሌያችን ሚኒሻ ለሆነው እንድመልሱ የሚያስችል ድርድር ጀምሬያለሁ። የማይመልሱ ከሆነ ካሉት ሚኒሾች አሸጋሽጌ ለአስር አለቃ መሐመድ ያሲን ቀበሌያችን ለማስታጠቅ እንገደዳለን ብለዋል። በዚህም መሠረት በሁለታቸው መካከል ተፈጥሮ የነበረውን አለመግባባት ወደቀደመው ፍቅር፣ሰላምና አንድነት በተቋቋመው የሐገር ሽማግሌዎች(አባጋሮች) የተፈታ ሲሆን የሐገር ሽማግሌዎች መሳሪያውን ወረዳ እንድመልስ በአጽንኦት ገልጸዋል። ወረዳው የአስር አለቃ መሐመድ ያሲንን መሳሪያ የማይመስል ከሆነ የምስራቅ ጉትን መላው ህዝብ ገዝቶ ለማስታጠቅ እንደሚገደድ አስምረው ተናግረዋል። የምስራቅ ጉትን ከመንደር 15 (ለጋ ሐዊ) ቀበሌ ጀምሮ እስከ አሙሩ ጃርቴ ጃርዴጋ ፊንጫዋ ስኳር ፋብሪካ የሚዘልቅ ሲሆን የሁሉም አከባቢ የአማራ ሚኒሻ አባላቶችና የአማራ የፖለቲካ አመራሮች ህዝቡን በማስተባበር ከእዙ ሐላፊ አዛዥ በኩል የሚተላለፈውን የሚያስፈጽሙ ሲሆን ሁሉም በጋራ የሚሰለፉበት ምህዳር ነው፤ ሲሉ ገልጸዋል። በምስራቅ ጉትን እዝ ስር የሚገኙ አከባቢዎች 80%ቱ የሆሮጉድሩ ወለጋ ዞን አከባቢዎች ሲሆኑ 20%ቱ የምስራቅ ወለጋ ዞን ይገኝበታል ሲሉ የእዙ ሐላፊ አስር አለቃ መሐመድ ያሲን ለአጉልዞ ጥያቄ ገልጸዋል። ከነዚህም መካከል፦ * ለጋ ሐዊ መ.15 ቀበሌ * ቱሉጋና ከተማ * መንደር 24 ቀበሌ * መንደር 25 ቀበሌ * አሩሲ ቀበሌ * ጋሬሮ ቀበሌ * ትጌ ቀበሌ * ጨቆርሳ * ወባንጭ ቀበሌ * ጎርቴ ቀበሌ * ቱሉ ላፍቱ ቀበሌ * ጨሩ፣ ጋሌሳ * ደቢስ ቀበሌ * ቱሉዋዩ ከተማ * ሐሮ ሾጤ ቀበሌ * ሰቀላ፣ ሳንቃ፣ * ደርጌ ኮትቻ ቀበሌ * ሻምቡ ከተማ፣ ፊንጫዋ * ጃርቴ ጃርዴጋ ቀበሌ * ጫንጮ ቀበሌ፣ ጉልማ ከተማ፣ ለጋሐድ፣ ጫልቲ፣ ብጅት እስከ አሊ ጎራ ማዶ የዘለቀ * በመንደር 23፣ መ.16፣17.18 * ቆጨራ፣ባታ ማሪያም፣ መድሐኒዓለም * ሉጎ ከተማ፣ አድስ አለም፣ * ወጤ(መርካቶ) በምስራቅ ወለጋ በሲቡስሬ ወረዳ እስከ ሳሲጋ ወረዳ ድንበርተኛ አከባቢዎች ድረስ * መንደር 20ቀበሌ *መንደር 21 ቀበሌ እና * ዳልቾ ቀበሌ፣ ጎርፌ፣ ምንጭሬ በሚባሉ አከባቢዎች የዘለቀ የምስራቅ ጉትን አከባቢዎች የሚገኙ የአማራ ማህበረሰብ ህዝቦች በአራቱም ማእዘናት ከሚገኙት የአከባቢው ማህበረሰቦች ጋር በስልክ በመለዋወጥ መረጃዎችን በመቀባበል ለእዞቹ ሐላፊዎች በመደወል በተጠቀሰው አከባቢዎች በተዋረድ ላለው የአከባቢው የሚመለከታቸው የስራ ሐላፊዎች በኩል ተፈጻሚ እንደሚሆን ተገልጿል። አስር(፲) አለቃ መሐመድ ያሲን ይህንን አስመልክቶ በመላው አለም ለሚገኘው ማህበረሰብ ጥሪ አስተላልፈዋል፥ የተከበራችሁ በመላው አለም የምትኖሩ ኢትዮጵያን እና ትውልደ ኢትዮጵያን በሙሉ የከበረ ሰላምታዬን እያቀረብኩ፦ እንደሚከተለው ሐሳቤን አቀርባለሁ። እንደሚታወቀው በሐገራችን ኢትዮጵያ በየጊዜው መልኩን እየቀያየረ በሚነሳው የእርስ በእርስ ግጭት በመንግሥት በኩል እልባት ይገኝለታል ተብሎ ተስፋ ቢጣልበትም ከጊዜ ወደጊዜ የጅምላ ጭፍጨፋው በአማራ ማህበረሰብ ላይ የከፋ ሆኗል። ስለሆነም በመላው አለም የምትገኙ እንድሁም በሐገር ውስጥ በተለያዩ ምክንያት ከወለጋ የለቀቃችሁ የአማራ ማህበረሰብ ህዝቦች በወለጋ በሚገኙ የፖለቲካ አመራሮች የመከፋፈል ስልት ጊዜው አልቆ እነሆ ዳግም ላንለያይ ተማምለን ታረቀናል። የጅምላ ጭፍጨፋውን ለመመከት ያስችላል ያልነውን ሁሉ ተጠቅመን ሁላችንም በየአካባቢያቸው ወጣቶች፣ ሰቶችና እድሜያቸው ለውትድርና ብቁ የሆነ ሁሉ በዚህ ታሪካዊ በሆነ እንደህዝብ ሊያጠፋን የመጣውን የምንመክትበት ሰዓት በመሆኑ ሁሉም በዚህ ስልጠና ገብቶ እንድሰለጥኑና በተለያዩ ስርዓት ውስጥ ወታደር የነበራችሁ በጡረታም ይሁን በስርዓት ብልሽት ምክንያት ውትድርናችሁን ለቃችሁ በወለጋ በአንገር ጉትንና በዙሪያው የምትገኙ ሁሉ ከእኛ በጋራ በሚሰጠው ስልጠና ሙያችሁን፣ ልምዳችሁንና ተሞክሮዎቻችሁን ታካፍሉን ዘንድ ተጋብዛችኋል። በሌሎች የአለማችን ክፍል የምትገኙ ደግሞ በየቀኑ ከምትሰሙት የጭፍጨፋ ዜና ለመትረፍ በሚያስችለው እራስን የመከላከል ተፈጥሯዊ ሰብዓዊ መብት ላይ ከጎናችን በሐሳባችሁ፣ በገንዘባችሁና በእውቀታችሁ ታግዙን ዘንድ ለማሳሰብ እንወዳለን። © አጉልዞ ጥያቄ ለፈጣንና አዳዲስ መረጃዎች የአይበገሬዎቹ ልሳን:- Youtube:- https://www.youtube.com/channel/UCPmgFzP2ZPmdGjHxXjigJaw Facebook:- https://www.facebook.com/asharamedia24 ቴሌግራም:- https://t.me/asharamedia24

Source: Link to the Post

Leave a Reply