በአንገር ጉትን ከተማ አማራን በማሰር ማህበራዊ እረፍት የመንሳቱ ዘረኛ አሰራር አሁንም ተጠናክሮ ስለመቀጠሉ ተገለጸ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ታህሳስ 12 ቀን 2015 ዓ/ም…

በአንገር ጉትን ከተማ አማራን በማሰር ማህበራዊ እረፍት የመንሳቱ ዘረኛ አሰራር አሁንም ተጠናክሮ ስለመቀጠሉ ተገለጸ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ታህሳስ 12 ቀን 2015 ዓ/ም አዲስ አበባ ሸዋ በምስራቅ ወለጋ ዞን ከአንገር ጉትን ከተማ ለአማራ ሚዲያ ማዕከል (አሚማ) እየደረሰ ያለው መረጃ እንደሚያመለክተው መከላከያ ከገባበት በተለይም ከህዳር 25/2015 ጀምሮ አማራዎች ተከታታይ እስርን ጨምሮ ሁለንተናዊ እረፍት እየተነሳ ነው። ታህሳስ 9/2015 አዲስ መከላከያ ሰራዊት መግባቱ ቢነገርም ልክ የቀደው ሲሰራው እንደነበረው ለአሸባሪው ሸኔ ጥይት ሲያቀብሉ ከነበሩ ሚሊሾች የተሳሳተ መረጃ በመቀበል ማሰሩን ቀጥሎበታል ብለዋል። ታህሳስ 10/2015 በአንገር ጉትን ከተማ የኦሮሞ ሚሊሾችንና የልዩ ኃይሎችን ጥቆማ በመቀበል:_ 1) ሲሳይ ገበዬሁ እና 2) መሀመድ የተባሉ እና ሌሎች አማራዎች መታሰራቸው ተገልጧል። ከህዳር 25/2015 ጀምሮ በርካታ አማራዎች ሆንተብሎ በሚሰጥ የተሳሳተ መረጃ የአማራ ሚሊሾች እና አርሶ አደሮች በገፍ መታሰራቸው ይታወቃል። ነዋሪዎች እንደሚሉት ከአሸባሪው ኦነግ ሸኔ ጋር ሲተባበሩ የነበሩ አካላት በህግ ፊት መቅረብ ሲገባቸው እነሱ አሳሪ እና አሳሳሪ ለመሆን በቅተዋል ነው ያሉት። አማራ ሚዲያ ማዕከል (አሚማ) ከተለያዩ ምንጮች እንዳጣራው ለህዳር 25/2015 ጀምሮ በምስራቅ ወለጋ አንገር ጉትን ከተማ በግፍ ከታሰሩት አማራዎች መካከል በከፊል:_ 1) ወዳጀ አባተ፣ 2) አበበ አታላይ፣ 3) ኡመር መኮንን፣ 4) ሞላ ያለው፣ 5) ፈንቴ ያለው፣ 6) አህመድ ልጎ፣ 7) መሀመድ የኑስ፣ 8 ኡስማን አባቡ፣ 9) አብዲ ሙስጦፋ፣ 10) መሀመድ አማን፣ 11) አዳም ደጁ፣ 12) ነስሩ ሸሪፍ፣ 13) አታላይ ገዳሙ፣ 14) ጫኔ ገዳሙ፣ 15) ባንቴ ስንሻው፣ 16) ፍስሃ/አሰፋ ሞላልኝ፣ 17) ወዳጀ የኑስ፣ 18) መሀመድ እሸቱ፣ 19) አያልሰው ደስታ፣ 20) ከድር ሀሰን፣ 21) ውለታው አበበ፣ 22) አስቻለው ሁነኛው፣ 23) እንድሪስ ኡመር፣ 24) ሙሉቀን አንተነህ፣ 25) ወጣት ገብርሽ እና 26) ታረቀኝ በላቸው የተባሉ ነዋሪዎች ይገኙበታል።

Source: Link to the Post

Leave a Reply