You are currently viewing በአንገር ጉትን ከተማ እና አካባቢው የጥቃቱ ሰለባ የሆኑ አማራዎችን ማሰሩ ተጠናክሮ እንደቀጠለ ነው፤ ህዳር 29/2015 ብቻ በወረዳው የጸጥታ ዘርፍ ኃላፊ ጥቆማ ብቻ 7 ሰዎች፣ በድምሩ ከሰሞ…

በአንገር ጉትን ከተማ እና አካባቢው የጥቃቱ ሰለባ የሆኑ አማራዎችን ማሰሩ ተጠናክሮ እንደቀጠለ ነው፤ ህዳር 29/2015 ብቻ በወረዳው የጸጥታ ዘርፍ ኃላፊ ጥቆማ ብቻ 7 ሰዎች፣ በድምሩ ከሰሞ…

በአንገር ጉትን ከተማ እና አካባቢው የጥቃቱ ሰለባ የሆኑ አማራዎችን ማሰሩ ተጠናክሮ እንደቀጠለ ነው፤ ህዳር 29/2015 ብቻ በወረዳው የጸጥታ ዘርፍ ኃላፊ ጥቆማ ብቻ 7 ሰዎች፣ በድምሩ ከሰሞኑ ብቻ ከ17 በላይ አማራዎች በመከላከያ እየተያዙ ለፖሊስ ተላልፈው መሰጠታቸው ተገልጧል። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ህዳር 30 ቀን 2015 ዓ/ም አዲስ አበባ ሸዋ በምስራቅ ወለጋ ዞን አንገር ጉትን ከተማ እና አካባቢው ከህዳር 24/2015 ጀምሮ የተደራጀ በኦሮሚያ ልዩ ኃይል የሚመራ መንግስታዊ ጦር እና አሸባሪው ኦነግ ሸኔ ለቀናት ጦርነት በመክፈት በርካታ ንጹሃንን የገደሉበት እና በመቶ ሽህ የሚቆጠሩ አማራዎች የተፈናቀሉበት ነው። ከህዳር 24/2015 ምሽት ጀምሮ መከላከያ የገባ ቢሆንም የጥቃቱ ሰለባ የሆኑ አማራዎችን እያሳደዱ ማሰራቸውን ስለመቀጠላቸው ተሰምቷል። አካባቢውን አረጋጋለሁ ብሎ የገባው መከላከያ ሰራዊት የኦሮሚያ ልዩ ኃይልን በቁጥጥር ስር አውሎ ትጥቅ ሳያስፈታ የተፈናቀሉ አማራዎችን ወደ አንገር ጉትን ተመለሱ፤ ስትመለሱ ግን ትጥቅም፣ ማናቸውን ስለት ነገሮችንም ሆነ ዱላ እንዳትይዙ በማለት ከልክሏል ብለዋል የአማራ ሚዲያ ማዕከል (አሚማ) ከስፍራው ያነጋገራቸው ምንጮች። ይህን ተከትሎም ወደ አንገር ጉትን ከተማ ከገቡት አማራዎች መካከልም ለአማራው የተለዬ ጥላቻ ባለው እና ጀሌ ማድረግ በሚፈልገው በወረዳው የጸጥታ ዘርፍ ኃላፊ በኮማንደር ኩምሳ እና መሰሎቹ የተሳሳተ እና የሆንተብሎ አማራውን የማዳከም ጥቆማ እየተመሩ እስካሁን ባለን መረጃ ከ17 በላይ መታሰራቸውን በማወቃችን እኛም ለመሸሽ ተገደናል ነው ያሉት ምንጮች። የአንገር ጉትን ወረዳ የጸጥታ ዘርፍ ቢሮ ኃላፊ ኮማንደር ኩምሳ ህዳር 29/2015 የመከላከያ አዛዦች ባሉበት የኦሮሞ ተወላጆች ጋር ስብሰባ አድርጓል። በእለቱም በእነ ኮማንደር ኩምሳ እና መሰሎቹ የመድረክ ላይ ጥቆማ የመከላከያን እገዛ በመጠቀም በርካታ ተጽዕኖ ፈጣሪ የሆኑና ራሳቸውን ብሎም ንጹሃን ህጻናትንና ሴቶችን ይከላከላሉ ተብለው የሚታሰቡ የአማራ ተወላጆችን እያሳደዱ በማሰር ላይ ናቸው ተብሏል። በዚህም መሰረት ከህዳር 25/2015 ጀምሮ በመከላከያ እንዲያዙ ከተደረጉት ከ10 ሸላይ አማራዎች በተጨማሪ ህዳር 29/2015 በተደረገው ስብሰባ ብቻ 7 አማራዎች ተይዘዋል፤ ህዳር 30/2015 ደግሞ ተጨማሪ የታሰሩ እንዳሉ የተናገሩት የአሚማ ምንጮች እስካሁን ቢያንስ ከ17 በላይ የአንገር ጉትን አማራዎች ታስረዋል፤ ሙሉቀን አንተነህ የተባለውን የግል ታጣቂ ወደ ነቀምት አሳልፈው መውሰዳቸውንም አውስተዋል።

Source: Link to the Post

Leave a Reply