You are currently viewing በአንገር ጉትን ከተማ የአማራ ሚሊሾችና አርሶ አደሮች እየታሰሩ መሆኑ ተገለጸ፤ ከአስር በላይ አማራዎች የታሰሩ ሲሆን ከመካከላቸው ሁለት የሚሆኑት ተለይተው በመከላከያ ወደ ነቀምት መወሰዳቸው…

በአንገር ጉትን ከተማ የአማራ ሚሊሾችና አርሶ አደሮች እየታሰሩ መሆኑ ተገለጸ፤ ከአስር በላይ አማራዎች የታሰሩ ሲሆን ከመካከላቸው ሁለት የሚሆኑት ተለይተው በመከላከያ ወደ ነቀምት መወሰዳቸው…

በአንገር ጉትን ከተማ የአማራ ሚሊሾችና አርሶ አደሮች እየታሰሩ መሆኑ ተገለጸ፤ ከአስር በላይ አማራዎች የታሰሩ ሲሆን ከመካከላቸው ሁለት የሚሆኑት ተለይተው በመከላከያ ወደ ነቀምት መወሰዳቸው ነዋሪዎችን አስቆጥቷል። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ህዳር 29 ቀን 2015 ዓ/ም አዲስ አበባ ሸዋ በኦሮሚያ ልዩ ኃይል፣በአሸባሪው ኦነግ ሸኔ እና በአጋሮቻቸው ከህዳር 24/2015 በአማራ ላይ ይፋዊ የሆነ ጦርነት ተከፍቶበት የሰነበተው አንገር ጉትን አሁንም አልተረጋጋም። ምንም እንኳ በከተማው መከላከያ የገባ ቢሆንም የወረዳው የጸጥታ ዘርፍ ኃላፊ በመሆን ኮማንደር ኩምሳ የተባሉ ሰው የሚመሩት የኦሮሚያ ልዩ ኃይል እና ፖሊስ በአካባቢያቸው አልፎ የሚሄድ አማራ ካገኙ እያፈኑ እንደሚወስዱ ተገልጧል። በእነ ኮማንደር ኩምሳ ትዕዛዝ በእለተ እሁድ ህዳር 25/2015 ከጠዋቱ 3 ሰዓት ጀምሮ ከሶስት ልጆቹ እና ባለቤቱ እንዲሁም ከሁለት ጓደኞቹ ጋር በመኖሪያ ቤቱ ባለበት የዲሽቃ፣ የቦንብ እና የጥይት ናዳ የወረደበት አርሶ አደር ሙሉቀን አንተነህ ይባላል። መኖሪያ ቤቱም በአንገር ጉትን ከተማ ከፖሊስ ጣቢያው 200 ሜትር በተለምዶ አሮጌ ከተማ በሚባል አካባቢ ነው። ለአማራ ተቆርቋሪ እና እውነትን የሚጋፈጥ ጀግና መሆኑ በተመሰከረለት በአቶ ሙሉቀን አንተነህ መኖሪያ ቤት ከርቀት በዲሽቃ ከመመታቱ በተጨማሪ የተወረወረው ቦንብ ሳይፈነዳ በመቅረቱ የእሱን፣ የቤተሰቦችንና የጓደኞቹን ህይወት ለመታደግ ተችሏል በወቅቱ የተደራጀ ጥቃት በተከፈተበት መኖሪያ ቤቱ ውስጥ የነበሩትም:_ 1) አቶ ሙሉቀን አንተነህ፣ 2) ነፍሰጡር ባለቤቱ ወ/ሮ ጸሀይነሽ፣ 3) ሶስት ልጆቻቸው ( ዕድሜዋ 4 ዓመት የሆናት የኬጅ ተማሪ ሴት፤ የ7 ዓመት ልጅ እና የ10 ዓመት የታመመ ልጃቸው)፣ 4) ሁለት ጓደኞቹ በድምሩ 6 ሰዎች መከላከያ ደርሶ በማስቆሙ ከጥቃቱ ተርፈዋል ተብሏል። መከላከያ እነ አቶ ሙሉቀን ጨምሮ ከአስር በላይ አማራዎችን በተፈናቀሉ ሰዎች ቤት አድርጎ ሲጠብቃቸው ከሰነበተ በኋላ በበላይ አካል ለምርመራ ይፈለጋሉ በማለት እንደ ምንጮች ከሆነ 1) አቶ ሙሉቀንን እና 2) አቶ ባንቴን ህዳር 28/2015 ለይቶ ወደ ነቀምት ወስዷቸዋል። አቶ ባንቴን ወደ ጣቢያ መልሰዋቸዋል የሚልም አለ። ቀሪዎችን ደግሞ ለአንገር ጉትን ፖሊሶች አስረክቧል። የአንገር ጉትን አማራዎችም በሁኔታው ደስተኛ አይደሉም። ከቅሬታቸው መካከልም:_ 1) አቶ ሙሉቀን አንተነህ ወደ ነቀምት በሚል መወሰዳቸው ለልዩ ኃይሉ እና ለፖሊስ ሊሰጡብን ነው፤ እነሱ ደግሞ ሊገድሏቸው ይችሏል የሚለውና 2) ቀሪዎቹ እስረኞች ደግሞ እንገድላቸዋለን በሚል የቡድን መሳሪያ እና ቦንብ ሲጥሉባቸው ለነበሩ ልዩ ኃይሎች እና ፖሊሶች ተላልፈው በመሰጠታቸው ይገድሉብናል በሚል ድርጊቱን ተቃውመዋል። ከሰሞኑ ከታሰሩት ከአስር በላይ አማራዎች መካከል:_ 1) ሙሉቀን አንተነህ፣ 2) አቶ ባንቴ፣ 3) ወጣት ገብርሽ፣ 4) አቶ አሸብር፣ 5) አባ ወዳጀ አባተ እና ሌሎች ስማቸው ያልታወቁ የአማራ አርሶ አደሮች ከሰሞኑ ተይዘው በእስር ላይ ይገኛሉ። አሁንም በግፍ እየታሰሩ የሚገኙ ሰላማዊ የአማራ አርሶ አደሮች በአስቸኳይ እንዲለቀቁ በነዋሪዎች ተጠይቋል። ፎቶው_የሙሉቀን አንተነህ ነው። ከአጉልዞ ጥያቄ የፌስ ቡክ ገጽ የተገኘ።

Source: Link to the Post

Leave a Reply