በአዋሽ ብሄራዊ ፓርክ የሚገኘው ሳላ የመጥፋት አደጋ ተጋርጦበታል ተባለ

ድርቅ እና ህገወጥ ሰፈራ ተከትሎ በአዋሽ ብሄራዊ ፓርክ የሚገኝ የሳላ መንጋ እየተመናመነ እንደሚገኝ ተገልቷል፡፡

በፓርኩ ውስጥ 350 ሳላ መኖሩን የአዋሽ ብሄራዊ ፓርክ ሃላፊ አደም መሀመድ ተናግረዋል፡፡

ከ55 ዓመታት በፊት የተቋቋመው የአዋሽ ብሔራዊ ፓርክ መለያ እንደሆነ እና ፓርኩ ለመጀመሪያ ጊዜ ሲቋቋም ለሳላ ትኩረት ተሰጦት ለመጠበቅ እንደነበር ተገልጸል፡፡

ፓርኩ ሲቋቋም 5 ሺህ ሳላ እንደነበር የገለጹት ሃላፊው ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ ግን በከፍተኛ ሁኔታ ሳላ መንጋ ላይ የመመናመን ሁኔታ እየተስተዋለ እንደሚገኝ ተናግረዋለል፡፡

በፓርኩ 81 የተለያየ አይነት ዝርያ የሚገኝ ሲሆን አንበሳ፣ ነብር፣ አጋዘን እና ሳላን ጨምሮ የተለያዩ 455 አዋፋት እንደሚገኙ ተነግሯል፡፡

የተፈጥሮ እና የሰው ሰራሽ አደጋ እየተበራከተ እንደሚገኝ የተገለጸ ሲሆን፤ ድርቅ እና ህገወጥ ሰፈራ ተከትሎ በፓርኩ ሚገኙ የዱር እንስሳት ላይ ጉዳት የሚደርሰውን ጉዳት ለመከላከል በፓርኩ ጽፈት ቤት ጥበቃ እየተከናወነ ይገኛል ብለዋል፡፡

በእሌኒ ግዛቸው

መጋቢት 05 ቀን 2016 ዓ.ም

Facebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Source: Link to the Post

Leave a Reply