በአውሮፓ የስደተኞችን የድንበር ላይ እንቅስቃሴ 24 የሚቃኝ አውሮፕላን ሊሰማራ ነው

https://gdb.voanews.com/97D6521C-EE2A-41D0-A1D5-CDD63EADDFD6_w800_h450.jpg

የአውሮፓ ህብረትን ድንበር የሚቆጣጠረው ድርጅት፣ ስደተኞች የሚገቡባቸውን የድንበር አካባቢዎች 24 ሰዓት የሚቃኝበት አውሮፕላን ለማሰማራት ማቀዱ ተገለጸ፡፡

ይህ የተገለጸው፣ ፈረንሳይ ወደ ድንበርዋ ስደተኞችን እያሰረጉ የሚያስገቡ የሰዎች አስተላላፊዎችን አድኖ በመያዝ፣ የአውሮፓ ህብረት አጋሮችዋ እንዲተባበሯት፣ ግፊት ማድረጓን ትናንት እሁድ ባስታወቀችበት ወቅት መሆኑን አጃንሳ ፍራንስ ፕሬስ ዘግቧል፡፡

ውሳኔው የመጣው ከአምስት ቀን በፊት 27 የሚሆኑ ስደተኞች፣ ውሃ ውስጥ ስጥመው የመሞታቸው ዜና ከተነገረ በኋላ ነው፡፡

ይህንም ተክትሎ፣ የፈረንሳይ፣ የጀርመን ፣የኔዘርላንድ እና የቤልጅየም የስደተኞች ጉዳይ ባለሥልጣናት፣ ፈረንሳይ ውስጥ ተገናኘተው መክረዋል፡፡

እንግሊዝን ባገለለው የአራቱ አገሮች ስብሰባ፣ ለስደተኞች የመንሳፈፊያ ጃኬት የሚያቀርቡና በጀልባ የሚያጓጉዙ ህገወጥ ቡድኖችን አድኖ ለመያዝ ትብብራቸውን ማጠንከራቸውን ገልጸዋል፡፡

27ቱ ሰዎች የሞቱት ከፈረንሳይ ወደ እንግሊዝ ባለው የባህር ላይ መተላለፊያ መስመር መሆኑን ተነገሯል፡፡

በዚህ ዓመት ብቻ ወደ 26ሺ የሚጠጉ ስደተኞች ከፈረንሳይ ወደ እንግሊዝ በጀልባ ቀዝፈው መግባታቸውም ተመልክቷል፡፡

ይሁን እንጂ ፈረንሳይ እኤአ በ2020 80ሺ የሚጠጉ የፖለቲካ ጥገኝነት ጠያቂዎችን ስታስተናግድ እንግሊዝ የተቀበለችው ወደ 27ሺ የሚደርሱትን ብቻ መሆኑም ተገልጿል፡፡

Source: Link to the Post

Leave a Reply