በአውስትራሊያ በደረሰ ዝናብ በቀላቀለ ከባድ አውሎ ነፋስ የ9 ሰዎች ህይወት ማለፉ ተገለጸ፡፡በአውስትራሊያ ምስራቃዊ የባህር ዳርቻ ላይ በደረሰ ዝናብ በቀላቀለ ከባድ አውሎ ነፋስ የ 9…

በአውስትራሊያ በደረሰ ዝናብ በቀላቀለ ከባድ አውሎ ነፋስ የ9 ሰዎች ህይወት ማለፉ ተገለጸ፡፡

በአውስትራሊያ ምስራቃዊ የባህር ዳርቻ ላይ በደረሰ ዝናብ በቀላቀለ ከባድ አውሎ ነፋስ የ 9 ሰዎች ህይወት ማለፉን UPI ዘግቧል፡፡

አውሎ ነፋሱ የተከሰተው በአውስትራሊያ ምስራቃዊ ኩዊንስላንድ፣ ኒው ሳውዝ ዌልስ እና ቪክቶሪያ ግዛት ውስጥ ሲሆን የሞቱ ሰዎች የገና በዓልን ምክንያት በማድረግ በባህር ዳርቻው ሲዝናኑ የነበሩ ናቸው ተብሏል፡፡

ከዘጠኙ ሟቾች በተጨማሪ በ10 ሺዎች የሚቆጠሩ ነዋሪዎች ተፈናቅለዋል፡፡ የከባድ ዝናቡ ተከትሉ በተከሰተው ጎርፍ ምክኒያት በሺዎች የሚቆጠሩ ቤቶች መውደማቸው ተገልጿል።

ሰሞኑን በአከባቢው ከበድ ያለ ነፋስ እየተከሰተ በመሆኑ የአውስትራሊያ የሚቲዎሮሎጂ ቢሮ ነዋሪዎች ጥንቃቄ እንዲያደርጉ መልእክት አስተልፏል፡፡

በተከሰተው አደጋ ሞተዋል ከተባሉ ሰዎች መካከል የሁለቱ ግለሰቦች አስክሬን ከሜሪ ወንዝ ዳር መገኘቱን የኩዊንስላንድ ፖሊስ በዛሬው እለት አስታውቋል፡፡

መሳይ ገብረመድህን
ታህሳስ 17 ቀን 2016 ዓ.ም

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ወቅታዊ አዳዲስ መረጃዎችና ፕሮግራሞችን ለማግኘት ከታች ያሉትን ገፆቻንን ይጎብኙ ቤተሰብ ይሁኑ ።

Telegram https://t.me/ethiofm107dot8

Twitter https://twitter.com/EthioFM

YouTube https://www.youtube.com/@onelovebroadcast/videos

Facebook https://www.facebook.com/onelovebroadcast

Website https://ethiofm107.com/

Telegram (https://t.me/ethiofm107dot8

Source: Link to the Post

Leave a Reply