በአውስትራሊያ የሚኖሩ የወልቃይት፣ ጠለምትና ጠገዴ ተወላጆች የአንድ ነጥብ ሁለት ሚሊየን ብር ድጋፍ አደረጉ፡፡ አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ  ታህሳስ 21 ቀን 2013 ዓ.ም          አዲስ…

በአውስትራሊያ የሚኖሩ የወልቃይት፣ ጠለምትና ጠገዴ ተወላጆች የአንድ ነጥብ ሁለት ሚሊየን ብር ድጋፍ አደረጉ፡፡ አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ታህሳስ 21 ቀን 2013 ዓ.ም አዲስ…

በአውስትራሊያ የሚኖሩ የወልቃይት፣ ጠለምትና ጠገዴ ተወላጆች የአንድ ነጥብ ሁለት ሚሊየን ብር ድጋፍ አደረጉ፡፡ አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ታህሳስ 21 ቀን 2013 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ ድጋፉ በህግ ማስከበር ስራ ላይ ለሚገኘው የሃገር መከላከያ ሰራዊት፣ ለአማራ ልዩ ሃይልና ለአማራ የሚሊሻ አባላት እንደሚውልም ነው የተገለፀው፡፡ ድጋፉን ያደረጉት በአውስትራሊያ የሚኖሩ የወልቃይት፣ የጠለምትና የጠገዴ ተወላጆች ናቸው፡፡ በውስትራሊያ ነዋሪ የሆኑትና የድጋፉ አስተባባሪ ቄስ ጌትነት በቀለ የገንዘብ ድጋፉን ደረሰኝ ለጎንደር ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አቶ ሞላ መልካሙ አስረክበዋል፡፡ በርካታ የወልቃይት፣ የጠለምትና የጠገዴ ተወላጆች በጁንታው የትህነግ የግፍ አገዛዝ ተማረው በስደት በአውስትራሊያ እንደሚኖሩ የገለፁት ቄስ ጌትነት በህግ ማስከበር ስራ ላይ ለሚገኙት የሃገር መከላከያ ሰራዊት ፣ለአማራ ልዩ ሃይልና ሚኒሻ አባላት ያላቸውን አክብሮት ለመግለፅ ድጋፉ መደረጉን ተናግረዋል፡፡ በአውስትራሊያ ከተሞች የሚኖሩ የወልቃይት፣ የጠለምትና የጠገዴ ተወላጆች አንድ ሚሊየን 208ሽ 400 ብር ሚን ቢን አውስትራሊያ የምዕራፍ አቡነ ተክለ ሃይማኖት ምዕምናን 70ሽ 120 ብር በድምሩ አንድ ሚሊየን 218ሽ 520 ብር ድጋፍ ማድረጋቸውንም አስተባባሪው ገልፀዋል፡፡ የአካባቢው ተወላጆች በሞራል ፣በገንዘብና በቁስቁስ እያደረጉት ያለውን ድጋፍ አጠናክረው እንደሚቀጥሉም ጠቁመዋል፡፡ የጎንደር ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አቶ ሞላ መልካሙ በበኩላቸው የሃገር መከላከያ ሰራዊት ፣የአማራ ልዩ ሃይልና ሚኒሻ አባላት በከፈሉት መስዋትነት ህግ የማስከበር ስራውን በብቃት ተወጥተዋል፡፡ ህግ በማስከበር ስራ ላይ በመሳተፍ ላይ ለሚገኙት የሃገር መከላከያ ሰራዊት ፣ለአማራ ልዩ ሃይልና ሚኒሻ አባላት ላበረከቱት አስዋፅዎ በመደገፍም ከዚህ ቀደም በአውሮፓ ፣በአሚሪካና በአውስትራሊያ የሚኖሩ የአካባቢው ተወላጆች የ1 ነጥብ 7 ሚሊየን ብር ድጋፍ መደረጉን ገልፀዋል፡፡ አሁን ደግሞ ለሁለተኛ ጊዜ በአውስትራሊያ የሚኖሩ የወልቃይት፣ የጠለምትና የጠገዴ ተወላጆች 1 ነጥብ 2 ሚሊየን ብር በላይ ድጋፍ ማድረግ በመቻላቸው ምስጋና አቅርበዋል፡፡ ድጋፋቸው ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ያላቸውን ተስፋ የገለፁት ከንቲባው በጎንደርና በአካባቢው ልማት እንዲሳተፉም ጥሪ አቅርበዋል ሲል የጎንደር ከተማ ኮሙዩኒኬሽን ዘግቧል፡፡

Source: Link to the Post

Leave a Reply