You are currently viewing በአዲሱ አጠራር ሸገር ከተማ አስተዳደር የቀጠለው አድሎአዊ በሆነ መልኩ የዜጎችን ቤቶች የማፍረስ ተግባር ማህበራዊ ቀውስ ማስከተሉ ተገለጸ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ   መጋቢት 27 ቀን 20…

በአዲሱ አጠራር ሸገር ከተማ አስተዳደር የቀጠለው አድሎአዊ በሆነ መልኩ የዜጎችን ቤቶች የማፍረስ ተግባር ማህበራዊ ቀውስ ማስከተሉ ተገለጸ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ መጋቢት 27 ቀን 20…

በአዲሱ አጠራር ሸገር ከተማ አስተዳደር የቀጠለው አድሎአዊ በሆነ መልኩ የዜጎችን ቤቶች የማፍረስ ተግባር ማህበራዊ ቀውስ ማስከተሉ ተገለጸ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ መጋቢት 27 ቀን 2015 ዓ/ም አዲስ አበባ ሸዋ ቤቶቹን ማፍረሱ አድሎአዊና ጎሳን ለይቶ እንደሚፈጸም ማሳያ አለ የሚሉት አንድ አስተያየት ሰጪ ቤቶቹ ሲፈርሱ ማስጠንቀቂያ እንኳን እንደማይሰጥ ያብራራሉ፡፡ ሌላኛዋ ተፈናቃይ ቤቱ በሚፈርስበት ወቅት ቤቱን የሰሩበት ቆርቆሮ እንኳ እንዳይወስዱ ተከልክለው አካላዊ ድብደባም እንደተፈፀመባቸው አስረድተዋል፡፡ በአዲስ አበባ ዙሪያ እንደ አዲስ ከወራት በፊት በይፋ በተመሰረተው ሸገር ከተማ የቀጠለው ቤቶች ማፍረስ በርካታ የማህበረሰብ አካላትን ለከፋ የማህበራዊ ቀውስ እየዳረገ ነው ተባሏል። በተለይም በከተማው ከለገጣፎ ለገዳዲ ክፍለ ከተማ ከተለያዩ መንደሮች የሚፈናቀሉ የማህበረሰብ አካላት አስተያየታቸውን ሲሰጡ ያለምንም ቅድመ ማስጠንቀቂያና ካሳ ይከናወናል ያሉት የቤቶች ፈረሳው ተስፋ እንዳሳጣቸው ተናግረዋል፡፡ በኦሮሚያ ክልል በሸገር ከተማ እየተካሄደ ባለው ቤቶችን የማፍረስ እና በግዳጅ የማስነሳት ሂደት የጸጥታ ኃይሎች ተመጣጣኝ ያልሆነ የኃይል እርምጃ መውሰዳቸውን ደግሞ የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን ከሰሞኑ አሳውቋል። የአንድ ወር እመጫት መሆናቸውን የሚገልጹት ወ/ሮ ዘውድነሽ በሸገር ከተማ አስተዳደር ከለገጣፎ ለገዳዲ ክፍለ ከተማ ድሬ ተብሎ ከሚታወቅ አካባቢ ከ16 ዓመታት በፊት ተሰርቶ ላለፉት 8 ዓመታትም ሲኖሩበት የነበረው ቤታቸው ፈርሶ መውደቂያ ማጣታቸውን ይገልጻሉ፡፡ “በተለያዩ አገራት ተንከራትቼ ያፈራሁት አለኝ የምለውን ሙሉ ቅርስ ነው ያጣሁት” የሚሉት የሁለት ልጆች አሳዳጊ እናት በቀን ስራ የሚተዳደር ባለቤታቸውን ጨምሮ አሁን ላይ የከፋ ህይወት ላይ መውደቃቸውንም ያስረዳሉ፡፡ “ገና አራስ ነኝ፡፡ ወልጄ ገና በሳምንቴ ነው ቤቱ እላያችን ላይ የፈረሰው፡፡ ሁለት መቶ ካሬ ሜትር ላይ ያረፈ ቤት ነበረኝ፡፡ ለ16 ዓመታት ሰርቼ ላለፉት 8 ዓመታት ደግሞ እራሴ የኖርኩበት ነው፡፡ አሁን ዘመድ ቤት ወድቄያለሁ ለጊዜው፡፡” የካሰዲ ከሚባል ሰፈር መፈናቀላቸውን የሚያነሱት ስማቸው እንዳይጠቀስ የጠየቁን ሌላኛዋ ተፈናቃይ እንደተናገሩት። ቤቱ በሚፈርስበት ወቅት ቤቱን የሰሩበት ቆርቆሮ እንኳ እንዳይወስዱ ተከልክለው አካላዊ ድብደባም እንደተፈፀመባቸው አስረድተዋል፡፡ “ቆርቆሮየን እንኳ ላነሳ ሲል እስካሁን የትነበራችሁ በማለት በአፍራሾቹ በዱላ ተደብድቤያለሁ፡፡ አንድ የተሰጠኝ ቆርቆሮ እንኳ የለም፡፡ አሁን ጅብ እንዳይበላኝ ነው የሰው በረንዳ ላይ የተቀመጥኩኝ፡፡ ልጆች አሉኝ፡፡ የ85 ዓመት አባቴንም አስተዳድራለሁ፡፡ ተስፋ ያደረኩት ሁሉ እንደተቀማሁ ተሰምቶኛል፡፡ ቤቱ የአየር ካርታ አለው፡፡ ለልማት ብለው በሺዎች የሚቆጠሩ ብርም ከሰሞኑ እንኳ ሰብስበዋል፡፡ እራሱ የመንግስት አካል ነው በጎን ለልማት ብሎ ብር እየተሰበሰበ የሚያፈርስብን፡፡” ሲሉም ተናግረዋል። “አሁን ልጆች ትምህርት አቋርጠው ከጎረቤቶቻችን ጋር ተለያይተን ተበታትነናል፡፡ ይህ ግንባታ ህገወጥ ነው ከተባለ እስካሁን መንግስት የትስ ነበር ለምን ይህ ሁሉ እስኪሆንስ ተመለከታቸው፡፡” ሲሉ ሌላኛዋ እናት ሀናግረዋል። የቤቶቹ ፈረሳ አድሎአዊና ጎሳን ለይቶ እንደሚፈጸም ማሳያ አለ የሚሉት ሌላ አስተያየት ሰጪ ደግሞ ቤቶቹ ሲፈርሱ ማስጠንቀቂያ እንኳን እንደማይሰጥ ያብራራሉ፡፡ “ለዓመታት ነው በዚህ የኖርነው፡፡ የአካባቢው ማህበረሰብ ለዚህ ምስክር ነው፡፡ በርካታ ቦታዎች ያለማስጠንቂያ ነው የፈረሱት፡፡ ቤቶችን ማፍረሱ አሁንም ቀጥሎ ሰሞኑን የሚፈርሱ ቤቶች ላይ ምልክት ማስቀመጥም ተጀምሯል፡፡ ሰሞኑን ነው እንጂ የተወሰነውን የአካባቢው ገበሬ ቤት ያፈረሱት መጤ እያሉ ነው ሌላው ጎሳ ላይ እያተኮሩ ቤት የሚያፈርሱት፡፡ አሁን እንደ እድር ያለው ማህበራዊ መገልገያዎች ተበትኗል፡፡” ሲሉ ገልጸዋል። የሸገር ከተማ አስተዳደር ቤቶች በሚያፈርስበት ወቅት በአንዳንድ አካባቢዎች የተቃወሙና መንገድ የዘጉ ሰዎች በጸጥታ ኃይሎች ድብደባ እንደደረሰባቸውና በዚህም የአካል ጉዳት መድረሱን የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) ከሰሞኑ አስታውቋል። በአዲስ አበባ ዙሪያ ያሉ ስድስት ከተሞችን በማጣመር 12 ክፍለ ከተሞች እና 36 የወረዳ አስተዳደሮችን በማዋቀር በተመሠረተው ሸገር ከተማ የቤቶች ፈረሳ እና በግዳጅ ማስነሳትን ተከትሎ ቅሬታ እንደደረሰውም ኢሰመኮ ገልጧል። በፈረሳ ሂደቱ ተገቢ ልየታ ያልተደረገበት፣ ያለበቂ ቅድመ ማስጠንቀቂያ፣ አድሎአዊ እርምጃ ስለመኖሩም ኢሰመኮ በሪፖርቱ አካቷል። “ማስጠንቀቂያ ሳይሰጥ ቤቶች እንደሚፈርስ እና አድሎአዊነት እንዳለ ለሚዲያ ቦታውን ክፍት በማድረግ ማረጋገጥ ይቻላል” ሲሉም አንድ ተፈናቃይ አስተያየታቸውን ሰጥተዋል፡፡ ዶይቼ ቨሌ እንዳጋራው።

Source: Link to the Post

Leave a Reply