
በአዲሱ የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል በኦሮሙማው ስልቀጣ ምክንያት ቁጣ ተነሳ። ግንቦት 08 ቀን 2015 ዓ.ም አሻራ ሚዲያ ፣ አዲሱ የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል በኦሮሙማው ስርአት ስልቀጣ ስር መውደቁን ተከትሎ ከፍተኛ ቁጣ ተነሳ፡፡ አዲሱ የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል ራሱን በኦሮሙማ መንግስት በቅርቡ የተደራጀ መሆኑ ይታወቃል፡፡ ይህንን ተከትሎ በክልሉ የተደራጀው ህዝባዊ ፖሊስ እና የፅጥታ አካላት የሚሊተሪ አርማቸው የኦነግ ዓርማ እንዲሆን ተደርጓል። ይህ መሆኑ ደግሞ በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝብ እና የፀጥታ አካላት በሰልቃጩ ኦሮሙማ ሥርዓት ላይ ከፍተኛ ተቃዉሞ እና ቁጣ አስነስቷል ተብሏል። የኦሮሙማው ኃይል በአዲሱ የደቡብ ምዕራብ ክልል በተለያዩ መዋቅሮች ጣልቃ በመግባት ጭምር የኦነግን ተልዕኮ እየፈስፈፀመ እንደሆነ ታውቋል። ይህ ደግሞ ከሰልሉን ወደ ለየለት ስልቀጣ ውስጥ ከቶታል ተብሏል። ለፈጣንና አዳዲስ መረጃዎች አሻራ ሚዲያ የአይበገሬዎቹ ልሳን:- // Youtube:- https://www.youtube.com/channel/UCPmgFzP2ZPmdGjHxXjigJaw // Facebook:- https://www.facebook.com/asharamedia24 // ቴሌግራም:- https://t.me/asharamedia24
Source: Link to the Post