በአዲስ አበባና አካባቢው የአሸባሪውን ቡድን ተልዕኮ ለማሳካት የሚንቀሳቀሱ በርካታ ተጠርጣሪዎችና ጦር መሳሪያዎች በቁጥጥር ስር ውለው ምርመራ እየተጣራባቸው እንደሆነ ተገለፀ። አማራ ሚዲያ…

በአዲስ አበባና አካባቢው የአሸባሪውን ቡድን ተልዕኮ ለማሳካት የሚንቀሳቀሱ በርካታ ተጠርጣሪዎችና ጦር መሳሪያዎች በቁጥጥር ስር ውለው ምርመራ እየተጣራባቸው እንደሆነ ተገለፀ። አማራ ሚዲያ ማዕከል ህዳር 2 ቀን 2014 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ ህዳር 1 ቀን 2014 ዓ.ም በአዲስ አበባና አካባቢው የአሸባሪውን ቡድን የሽብር ተልዕኮ ለማሳካት የሚንቀሳቀሱ በርካታ ተጠርጣሪዎችና ጦር መሳሪያዎች በቁጥጥር ስር ማዋሉን የመዲናዋ የጸጥታ ግብረ ሃይል አስታወቀ። የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ የወንጀል መከላከል ዘርፍ ኃላፊ ምክትል ኮሚሽነር ጀኔራል መላኩ ፋንታ እና የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ጌቱ አርጋው በጋራ መግለጫ ሰጥተዋል። በመግለጫቸው በአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ መሰረት በወንጀል መከላከልና ምርመራ ዘርፍ በመዲናዋ በርካታ ውጤታማ ተግባራት መከናወናቸውን ገልፀዋል። በሰሜን ኢትዮጵያ ግፎችን እየፈጸመ ያለው አሸባሪው የሕወሃት ቡድን ሸኔን ጨምሮ የተለያዩ ፀረ ሰላም ኃይላትን በማደራጀት የሽብር ተልዕኮውን ለማስፋት እየተንቀሳቀሰ መሆኑን ገልፀዋል። አሸባሪው ህወሃት በአዲስ አበባና ዙሪያዋ ከሸኔ ጋር በመተባበር የሽብር ተልዕኮውን በማስፋፋትና የአገር ህልውናን አደጋ ላይ ለመጣል እየተንቀሳቀሰ ቢሆንም በመዲናዋና አካባቢዋ የፀጥታ ችግር እንዳይፈጠር የተቋቋመው ግብረ ኃይል አበክሮ እየሰራ እንደሆነ ገልፀዋል። የሽብር ቡድን የመለመላቸው የሽብር ተልዕኮ የተቀበሉ በርካታ ተጠርጣሪዎች እንዲሁም የተለያዩ ጦር መሳሪያዎች በቁጥጥር ስር ውለዋል። በተለያዩ ተቋማት የተሰገሰጉ እና በአካባቢው ሽብር የሚነዙ ፀጉረ ልጉጦች ከነሀሰተኛ መታወቂያቸው መያዛቸውን፤ የጎዳና ተዳዳሪ በመምሰልና በቤተ እምነቶች በፀበል ቦታ የሀይማኖት አባትና ፀበልተኛ በመመሰል የገቡ ተልዕኮ ወስደው የተሰማሩ ግለሰቦች በአሰሳ ተይዘው ጉዳያቸው በህግ እየተጣራ እንደሆነ ጠቁመዋል። በተካሄደው የፍተሻና ብርበራ ኦፕሬሽን የመከላከያን ጨምሮ የፌዴራልና የክልል ፀጥታ ኃይላት አልባሳት፣ ማዕረግና መለዮዎች፣ የጦር ሜዳ መነጽር፣ ኮምፓስ፣ ጂፒየስ፣ ተተኳሽ የቡድኑ መሳሪያ የአገር ውስጥና የውጭ አገር ገንዘቦች ይገኙበታል። ለሽብር ተልዕኮ የሚያገለግሉ የሳተላይት ስልኮች፣ ሬዲዮ፣ ገመድ አልባ ስልኮች፣ ላፕቶፖች፤ የፎቶ ካሜራዎችም በቁጥጥር ስር ውለዋል። በፍተሻው ከተያዙ የጦር መሳሪያዎችና ተተኳሾች በተጨማሪ የተለያዩ ፈንጅና መሰል ነገሮችን በፔስታል እየተጠቀለሉ በበጎዳ ላይ ተጥለው መያዛቸውን ገልጸዋል። ህብረተሰቡ ከፀጥታ ሃይሉ አቅም በላይ የሆነ አካል አለመኖሩን በመረዳት አካባቢውን በንቃት በመጠበቅ መረጃ በመስጠት ከፀጥታ ሃይሉ ጎን በመሆን እያደረገ ስላለው ድጋፍ ምክትል ኮሚሽነር ጀኔራል መላኩ ፋንታ እና የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ጌቱ አርጋው የላቀ ምስጋናቸውን አቅርበው ህብረተሰቡ አሁንም ቀጣይም ጠቃሚ ድጋፉን አጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት አሳስበዋል ሲል የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታውቋል፡፡

Source: Link to the Post

Leave a Reply