በአዲስ አበባና ዙሪያዋ በትጥቅ የታገዘ ሁከት ለመፍጠር “በህቡዕ ሲንቀሳቀሱ የነበሩ” ተጠርጠሪዎች መያዛቸው ተገለጸበአዲስ አበባ ከተማ እና አዋሳኝ አካባቢዎች በትጥቅ የታገዘ ሁከት እና ብጥብ…

በአዲስ አበባና ዙሪያዋ በትጥቅ የታገዘ ሁከት ለመፍጠር “በህቡዕ ሲንቀሳቀሱ የነበሩ” ተጠርጠሪዎች መያዛቸው ተገለጸ

በአዲስ አበባ ከተማ እና አዋሳኝ አካባቢዎች በትጥቅ የታገዘ ሁከት እና ብጥብጥ ለመፈፀም በህቡዕ ሲንቀሳቀሱ የነበሩ 50 ተጠርጠሪዎች በቁጥጥር ሥር መዋላቸውን መንግሥት አስታወቀ።

የተጠርጣሪዎቹን በቁጥጥር ስር መዋል ይፋ ያደረገው የጸጥታና ደኅንነት የጋራ ግብረ ኃይል ቡድኑ “በአማራ ክልል የነበረው የጥፋት ሴራ ስለከሸፈበት እኩይ ዓላማውን ወደ ማዕከል በማምጣት የሁከትና የሽብር ተልዕኮው ለመፈጸም ተንቀሳቅሷል” ብሏል።

መግለጫው አክሎ፤ ይህ የተደራጀ ቡድን ዋና ማዕከሉን አዲስ አበባ እና በአማራ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን ምንጃር ሸንኮራ በማድረግ በመዲናዋ እና አዋሳኝ አካባቢዎች በማድረግ ሲሰራ ነበር ብሏል።

ቡድኑ በአዲስ አበባ በተለያዩ አካባቢዎች “አባላት መመልመልና እና ሎጀስቲክስ የማደራጀት ሥራዎችን ሲያከናውን” መቆየቱ ተመላክቷል።

የብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት ባለፉት አምስት ወራት በቡድኑ ላይ ክትትል ሲያደርግ ቆይቷል የተባለ ሲሆን ለቡድኑ ተልዕኮ የሰጡት በአማራ ክልል የሚንቀሳቀሱ ኃይሎች መሆናቸውም ተዘግቧል።

የጸጥታና ደኅንነት የጋራ ግብረ ኃይል፤ ቡድኑ ከጦር መሳሪያዎች፣ ተተኳሾች፣ ቦንቦች፣ ተቀጣጣይ ቁሶች፣ ለቀለብ የሚውሉ ግብአቶች፣ የተለያዩ ሀገራት የገንዘብ ኖቶች፣ የባንክ ደብተሮች እና የተለያዩ ሰነዶች ጋር መያዛቸውን አስታውቋል፡፡

ግብረ ኃይሉ በቁጥጥር ከዋሉት መካከል ስንታየሁ ንጋቱ የተባለው የቡድን መሪ እንደሚገኘበት የገለጸ ሲሆን የሴራው ዋነኛ ጠንሳሾች ሻለቃ ዳዊት ወልደጊዮርጊስ፣ ሀብታሙ አያሌው እና መሳይ መኮንን እንዲሁም አገር ውስጥ በሚገኘው እስክንድር ነጋ የሚመራ ነው ብሏል።

በተጨማሪም ይህ ቡድን በአሁኑ ወቅት በሕግ ቁጥጥር ሥር በሚገኙ ዶ/ር ወንድወሰን አሰፋ፣ ረዳት ፕሮፌሰር ሲሳይ አውግቸው እና ዮርዳኖስ ዓለሜ የሚመራ መሆኑን መግለጫው ጠቁሟል።

የጸጥታና ደኅንነት የጋራ ግብረኃይል፤ “እኩይ ዓላማ ያላቸው የጥፋት ኃይሎች የእምነት ቦታዎችን ለጥፋት ተልዕኮ እየተጠቀሙበት በመሆኑ ከእምነቱ ስርዓት ውጭ የሚደረጉ እንቅስቃሴዎች ላይ ቁጥጥርና እና የእርምት እርምጃዎች እንዲወሰድ” ጥሪ አቅርቧል፡፡

ግብረ ኃይሉ የጥፋት ሴራዎች ከፀጥታና ደኅንነት አካላት ስለማያመልጡ ግለሰቦች ከጥፋት መንገዳቸው ተመልሰው የሰላም አማራጭ እንዲጠቀሙ በመግለጫው ገልጧል።

ለዚህና መሰል የጥፋት ተልዕኮዎች መሳሪያ እየሆኑ ያሉ ንፁሃን ዜጎችም ራሳቸውን ከእንደዚህ ዓይነቱ ድርጊት እንዲቆጠቡ ሲል መልዕክት አስተላልፏል።

መጋቢት 11ቀን 2016 ዓ.ም

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ወቅታዊ አዳዲስ መረጃዎችና ፕሮግራሞችን ለማግኘት ከታች ያሉትን ገፆቻንን ይጎብኙ ቤተሰብ ይሁኑ ።

Telegram https://t.me/ethiofm107dot8

Twitter https://twitter.com/EthioFM

YouTube https://www.youtube.com/@onelovebroadcast/videos

Facebook https://www.facebook.com/onelovebroadcast

Source: Link to the Post

Leave a Reply