በአዲስ አበባ ለሚገኙ መምህራን እና የትምህርት ቤት አመራሮች የሙያ ብቃት ምዘና ከነገ ጀምሮ ይሰጣል። የሙያ ብቃት ምዘና ፈተናውን የከተማ አስተዳደሩ ትምህርት ቢሮ እና የትምህርትና ስልጠና…

https://cdn4.cdn-telegram.org/file/NbW1hMUruE5WGx2waL9xl8p8kkZlJrJeTaxqdOi-gVspNr45eyIIstWCeKeC8r3m3gC0wMP5SA8_c5sxuS3L5FyFciWTfk8pfOfgNNLI7ps6ENBowLze3_VKGP7xTG-KcRprjYKg2nDwgR5oomFNsJSQu-l4rdd_4rR_lxBVqfebwskrA9YtY6KObXys_RJUqojBiwK6DGzQYzbtqqlJ3rUz1G-RsRoNlKG5BmtIYfWSmcdlqIn5XfLQtV6ok3Ny7zG2Ewphl_FfdAI436mk0w6_8fqeod7KZf7woVnpPEooLJQl3gZGz6XKpDAvNtq_UN0gb_-6Dz2QglSS6oLNTQ.jpg

በአዲስ አበባ ለሚገኙ መምህራን እና የትምህርት ቤት አመራሮች የሙያ ብቃት ምዘና ከነገ ጀምሮ ይሰጣል።

የሙያ ብቃት ምዘና ፈተናውን የከተማ አስተዳደሩ ትምህርት ቢሮ እና የትምህርትና ስልጠና ጥራት ቁጥጥር ባለስልጣን በጋራ እንደሚሰጡት ተገልጿል።

ምዘናው በፈቃደኝነት ለተመዘገቡ 18,591 መምህራን እና የትምህርት አመራሮች ከነገ ሐሙስ ግንቦት 1/2016 ዓ.ም ጀምሮ በተመረጡ የመፈተኛ ጣቢያዎች መሰጠት ይጀምራል ተብሏል።

ተመዛኞች ስልክና የትኛውም አይነት የኤሌክትሮኒክስ ቁሶች ይዘው ወደ መፈተኛ ክፍል መግባት አይችሉም።

ተመዛኞች የታደሠ መታወቂያ በመያዝ ፈተናው ከሚጀምርበት ሰዓት (2:30) አንድ ሰዓት ቀደም ብለው በምዘና መስጫ ቅጥር ግቢ ውስጥ መገኘት ይኖርባቸዋል ተብሏል።

ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያዊያን

ሚያዝያ 30 ቀን 2016 ዓ.ም

Source: Link to the Post

Leave a Reply