በአዲስ አበባ መንግስትን እንዳይጠይቁ የተከለከሉ ከ300 በላይ ተፈናቃዮች እውቅና እና ድጋፍ ወደነፈጋቸው አቦምሳ ወረዳ እንዲመለሱ ተደረገ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ የካቲት 15 ቀን 2…

በአዲስ አበባ መንግስትን እንዳይጠይቁ የተከለከሉ ከ300 በላይ ተፈናቃዮች እውቅና እና ድጋፍ ወደነፈጋቸው አቦምሳ ወረዳ እንዲመለሱ ተደረገ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ የካቲት 15 ቀን 2014 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ ከኦሮሚያ ክልል ሆሮ ጉድሩ ዞን አቢ ደንጎሮ ወረዳ በአማራዊ ማንነታቸው የተፈናቀሉ ከ300 በላይ አማራዎች የካቲት 6 ቀን 2014 አዲስ አበባ መግባታቸው ይታወሳል። እነዚህ ከአርሲ ዞን አቦምሳ ወረዳ መርቲ ከተማ ከተፈናቀላችሁበት ዞንና ወረዳ ደብዳቤ ካላመጣችሁ አናውቃችሁም የተባሉ ከጅምላ ግድያ ሸሽተው ያመለጡ ተፈናቃዮች አዲስ አበባ ለሁለተኛ ጊዜ ቢመለሱም በአዲስ አበባ ፖሊስ ተይዘው በየካ፣በፈረንሳይ እና በጃንሜዳ ያለእረፍት ሲንከራተቱ ነበር። በመቀጠልም ያለምንም የመረጃ ልውውጥ የካቲት 14 ን 2014 ከአዲስ አበባ ወደ ደብረ ብርሃን ቢጫኑም “ቦታ የለም፣ በቂ እርዳታም የለም” በሚል ተቀባይነት አላገኙም፤ ኃላፊነቱን ወስዶ የሚደግፍ የመንግስት አካልም አልተገኘም። በዚህም የካቲት 14/2014 ሌሊቱን በአዲስ አበባ ፖሊስ ታጅበው ሸኖ ጫካ አድረው በማግስቱ ማለትም የካቲት 15/2014 አመሻሹን በአርሲ ዞን አቦምሳ ወረዳ መርቲ ከተማ ገብተዋል፤ የሚመለከተው የመንግስት አካላት እንዲረከባቸው ጥረት እየተደረገ መሆኑ ተሰምቷል። አዲስ አበባ ሆነው የፌደራል መንግስትን እንዳይጠይቁ የተከለከሉት እነዚህ ከ300 በላይ የሚሆኑ ወገኖች “ከተፈናቀላችሁበት አካባቢ ማስረጃ ካላመጣችሁ እውቅና እና ድጋፍ የላችሁም” በሚል ወደመለሳቸው አቦምሳ መርቲ ወረዳ ደርሰዋል። በአቦምሳ ወረዳ አንድ ቀበሌ ላይ አንድ መኪና በመበላሸቱ ከ20 በላይ ተሳፋሪዎች ጫካ ላይ መሆናቸው ተሰምቷል፤ ሌላ ተቀያሪ መኪና በአስቸኳይ እንዲደርስላቸው ጠይቀዋል።

Source: Link to the Post

Leave a Reply