በአዲስ አበባ መጪዎቹ 3 ወራት ውስጥ 400 አዲስ አውቶቢሶችን ወደስራ ለማስገባት እየሰራ መሆኑን የከተማዋ ትራንስፖርት ቢሮ አስታወቀ፡፡የአዲስ አበባ ከተማ ትራንስፖርት ቢሮ ከዚህ ቀደም 5…

በአዲስ አበባ መጪዎቹ 3 ወራት ውስጥ 400 አዲስ አውቶቢሶችን ወደስራ ለማስገባት እየሰራ መሆኑን የከተማዋ ትራንስፖርት ቢሮ አስታወቀ፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ ትራንስፖርት ቢሮ ከዚህ ቀደም 560 አውቶቢሶችን ወደስራ ማሰማራቱን ገልፆ በመጪዎቹ 3 ወራት ውስጥ ተጨማሪ 400 አዲስ አውቶቢሶችን ለማስገባት እየሰራ መሆኑን ነው የገለፀው፡፡

ባሳለፍነው ሳምንት 560 አውቶቢሶች ወደስራ ይገባሉ ተብሎ ሲጠበቅ የነበረ ቢሆንም በቅድሚያ 420 የሚሆኑ አውቶቢሶች ብቻ ነበሩ ስራ የጀመሩት፡፡

ቀሪዎቹ ከዉል ጋር ተያይዞ በነበረ ችግር ምክንት የዘገዩ ሲሆን አሁን ላይ ሁሉም ወደስራ መግባታቸውን በአዲስ አበባ ከተማ ትራንስፖርት ቢሮ የህዝብ ግንኙነትና ኮሚኒኬሽን ጉዳች ዳይሬክተር አቶ አረጋዊ ማሩ ገልፀውልናል፡፡

አቶ አረጋዊ አክለውም የትራንስፖርት ችግሩን ለመፍታት ከዚህ አመት ጀምሮ 3 ሺህ ባሶችን ወደ ስራ ለማስገባት በሂደት ላይ መሆናቸውንም ነግረውናል፡፡

አሁን ላይ ወደስራ የገቡ አውቶቢሶችን አፈፃፀም በማየት በሂደት ላይ ካሉት 3 ሺህ አውቶቢሶች መካከል 400 ዎቹን እስከ ቀጣዩ ታህሳስ ወር ድረስ ተገጣጥመው ያለቁ አውቶቢሶች ካሉ ወደ ስራ እንዲገቡ በማድረግ ችግሩን ለመፍታት እየተሰራ መሆኑን ነው የገለፁልን፡፡

በሁሉአገር አተሮ
ጥቅምት 19 ቀን 2013 ዓ.ም

Source: Link to the Post

Leave a Reply