በአዲስ አበባ ማስክ የሚጠቀሙ ሰዎች ቁጥር ከ72 በመቶ ወደ 52 በመቶ ማሽቆልቆሉ ተገለጸ።በኢትዮጵያ የኮሮና ቫይረስ ዙሪያ ያለው መዘናጋት ከቀጠለ ካለን የጽኑ ህሙማን ክፍል አንጻር አሳሳቢ…

በአዲስ አበባ ማስክ የሚጠቀሙ ሰዎች ቁጥር ከ72 በመቶ ወደ 52 በመቶ ማሽቆልቆሉ ተገለጸ።

በኢትዮጵያ የኮሮና ቫይረስ ዙሪያ ያለው መዘናጋት ከቀጠለ ካለን የጽኑ ህሙማን ክፍል አንጻር አሳሳቢ መሆኑን የጤና ጥበቃ ሚንስቴር አስታውቋል።

የጤና ጥበቃ ሚንስትር ዶክተር ሊያ ታደሰ በወቅታዊ የኮሮና ቫይረስ መግለጫ በመስት ላይ ናቸው።

ዶክተር ሊያ ታደሰ በአዲስ አበባም ይሁን በክልል ከተሞች እየታየ ያለው መዘናጋት ከቀጠለ የጽኑ ህሙማን የምናስተኛበት ቦታ ላይበቃን ይችላል ብለዋል።

ይሄም አሳሳቢ ሆኖብናል ያሉት ሚንስትሯ
የማስክ አጠቃቀምን በተመለከተ በየሳምቱ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ጥናት ያደርጋል ብለዋል።

በዚህም ከሰኔና ሀምሌ ወር ባጠናነው ጥናት መሰረት አዲስ አበባ 75 በመቶ ህብረተሰቡ ማስክ ይጠቀም ነበር አሁን ላይ ግን ወደ 52 በመቶ ወርዷል።

በተመሳሳይም በክልል ከተሞች የማስክ አጠቃቀም ቀንሷል ሲል አክለዋል
ሜካኒካል የመተንፈሻ መሳሪያ ላይ ያሉ ህሙማን ቁጥር እየጨመረ እንደሆነ ተገልጿል።

የኮሮና ቫይረስ ክትባት ለማግኘት የሚያስችለንን በጤና ሚኒስቴር የሚመራ ግብረ ሀይል አቋቁመን ዝግጅት እያደረጉ መሆኑንም ሚንስትሯ ተናግረዋል ።

መጀመሪያ የሚከተቡና ቅድሚያ የሚሰጣቸው የህብረተሰብ ክፍሎችን መለየት ላይ እንሰራለን ብለዋል።

የጸጥታ ሀይሎ እድሜያቸው የገፉ ሰዎች መምህራን ቅድሚያ ከሚሰጣቸው የተለዩ ናቸው።

ክትባቱ ከመጣም በኋላ በጤና ስርአቱ ተጠብቆ ወደ ህብረተሰቡ ለማድረስ ስራም ይሰራል ብለዋል ዶክተር ሊያ
የአለም ባንክም ድጋፍ እንዲያደርግ ጠይቀናል ሲሉም አክለዋል።

አሁን ላይም ስለ ክትባቱ በቂ መረጃ ለህብረተሰቡ ለመስጠት የምንጀምረው ስራ ነው ተብሏል።

እስካሁን ባለው መረጃ 1ነጥብ 6ሚሊየን ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ምርመራ የተደረገላቸው ሲሆን 114 ሺህ በላይ ሰዎች ቫይረሱ እንደተገኘባቸው ከሚኒስቴሩ ያገኘነው መረጃ ያሳያል።

በመቅደላዊት ደረጀ
ታህሳስ 1 ቀን 2013 ዓ.ም

Source: Link to the Post

Leave a Reply