በአዲስ አበባ ቂርቆስ ክፍለ ከተማ ትናንትሌሊት በደረሰ የእሳት አደጋ ከ2 ሚሊየን ብር በላይ ንብረት ወደመ

በአዲስ አበባ ቂርቆስ ክፍለ ከተማ ትናንትሌሊት በደረሰ የእሳት አደጋ ከ2 ሚሊየን ብር በላይ ንብረት ወደመ

አዲስ አበባ፤ ታህሳስ 28፣2013(ኤፍ ቢ ሲ) በቂርቆስ ክፍለ ከተማ ትናንት ሌሊት በደረሰ የእሳት አደጋ ከ2 ሚሊየን ብር በላይ የሚገመት ንብረት መውደሙን የአዲስ አበባ የእሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን ገለጸ።

የኮሚሽኑ ህዝብ ግንኙነት ቡድን መሪ አቶ ጉልላት ጌታነህ÷ የእሳት አደጋው የተከሰተው በክፍለ ከተማው ወረዳ 11 መኮንኖች ክበብ በሚባለው አካባቢ ከሌሊቱ 8 ሰዓት ገደማ ነው ብለዋል።

በአደጋው 2 ሚልየን 300 ሺህ ብር የሚገመት ንብረት የወደመ ሲሆን÷ በሰው ህይወት ላይ ግን የደረሰ ጉዳት የለም ብለዋል።

የእሳት አደጋው በአንድ እንጨት ቤት፣ ጋራዥ ቤት እና በቶርኖ ቤት ላይ ከፍተኛ ጉዳት ማድረሱንም ገልጸዋል።

በጋራዡ ውስጥ ከነበሩት 5 መኪኖች መካከል ሁለቱ ሙሉ ለሙሉ ሲወድሙ ሶስቱ ከፍተኛ ጉዳት የደረሰባቸው ሲሆን የአደጋው መንስኤ ገና በመጣራት ላይ ነው ተብሏል፡፡

እሳቱን ለማጥፋት ከአካባቢው ማህበረሰብ ጋር በተደረገ ርብርብ 26 ሚልየን ብር የሚገመት ንብረት ለማዳን ተችሏልም ብለዋል።

በነገው እለት በሚከበረው የገና በዓልም የእሳት አደጋ እንዳያጋጥም ህብረተሰቡ ተገቢውን ጥንቃቄ እንዲያደርግ አቶ ጉልላት ማሳሰባቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

The post በአዲስ አበባ ቂርቆስ ክፍለ ከተማ ትናንትሌሊት በደረሰ የእሳት አደጋ ከ2 ሚሊየን ብር በላይ ንብረት ወደመ appeared first on Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C.

Source: Link to the Post

Leave a Reply