በአዲስ አበባ በሕገ ወጥ መንገድ ተከማችቶ የተገኘ ከ2 ሚሊዮን ጄሪካን በላይ ፓልም የምግብ ዘይት በቁጥጥር ስር ዋለ።በአዲስ አበባ ከተማ ንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ በተለምዶ ጀሞ ሚካኤል…

በአዲስ አበባ በሕገ ወጥ መንገድ ተከማችቶ የተገኘ ከ2 ሚሊዮን ጄሪካን በላይ ፓልም የምግብ ዘይት በቁጥጥር ስር ዋለ።

በአዲስ አበባ ከተማ ንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ በተለምዶ ጀሞ ሚካኤል ተብሎ በሚጠራው አካባቢ በልዩ ስሙ አንበሳ ጋራዥ በሚባለው ቦታ በሕገ ወጥ መንገድ ተከማችቶ የተገኘ ከ2 ሚሊዮን ጄሪካን በላይ ፓልም የምግብ ዘይት ዛሬ በቁጥጥር ስር ውሏል።

ከአካባቢው በደረሰ የህዝብ ጥቆማ የፌዴራል ፖሊስ እና የንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማና የወረዳ 2 አስተዳደር ለ2 ሳምንታት ባደረጉት ጥብቅ ክትትል በህሕገወጥ መንገድ የተከማቸው ዘይት በቁጥጥር ስር ሊውል ተችሏል ።

በከተማው የሚታየውን የኑሮ ውድነት ለመቆጣጠር አስተዳደሩ ልዩ ግብረሀይል በማቋቋም የንግድ ስርዓቱ ላይ ቁጥጥር እያደረገ ሲሆን የተያዘውም ዘይት በመንግስት አቅርቦት ለህብረተሰቡ ፍጆታ እንዲውል የቀረበ ነው።

በአካባቢው ህብረተሰብ፣በአመራሮችና በፀጥታ ሀይሎች የጋራ ቅንጅት የተወሰደው እርምጃ የሚመሰገን ነው።

በህጋዊ ነጋዴ ሽፋን የፍጆታ ዕቃዎችን በድብቅ እና በማከማቸት በከተማዋ የፍጆታ ዕቃዎች እጥረት እንዲፈጠር በማድረግ ማህበረሰቡን ለከፍተኛ ችግር የሚዳርጉ ነጋዴዎችን በማጋለጥ ሁሉም ባለድርሻ አካላት የበኩላቸውን ሚና መወጣት ይኖርባቸዋል ።

ኢትዮ ኤፍ ኤም የኢትዮጵያዊያን
የካቲት 6 ቀን 2013 ዓ.ም

Source: Link to the Post

Leave a Reply