በአዲስ አበባ በሚካሄደዉ የአፍሪካ ሕብረት ጉባዔ ላይ 35 ፕሬዝዳንቶችና 4 ጠቅላይ ሚኒስትሮች ይሳተፋሉ ተባለ፡፡በአፍሪካ ሕብረት ስብሰባ ላይ የ51 አገራት ልዑካን ቡድኖች እንደሚሳተፉ…

https://cdn4.telegram-cdn.org/file/fLYjllfNm2WO2MUw_UaepTT0Y0jvpcjLEbzUicMmB5PdWu-9B4gDzjg4PffYFmJq2HWfgQFuFpgYOrO58Np3NihQapGm-As5G_gvVQvCQC2wPGQHgT6dYgHJbvdqPaWL5ZinSrJAyAG3ck8gYQgGcknMUHMG-ljlfI7MyA2pCnkx-3bPvR6XhoIyDGm5E9QxHKK_Uakx8sIiLPYYZz8CxPHBM7wKczOjc3kuwP4PLAbqI9Ja_xpzgMsFnnSo-2tMNyaOk6HLeZGuigFWIFeEtf6tMxow2hfzE2FIpDusunMCJnssd-OeLsNQcG0UpKqvlkXbHN_E4pf0wn1Zw-QgLw.jpg

በአዲስ አበባ በሚካሄደዉ የአፍሪካ ሕብረት ጉባዔ ላይ 35 ፕሬዝዳንቶችና 4 ጠቅላይ ሚኒስትሮች ይሳተፋሉ ተባለ፡፡

በአፍሪካ ሕብረት ስብሰባ ላይ የ51 አገራት ልዑካን ቡድኖች እንደሚሳተፉ ታዉቋል፡፡
በመድረኩ ላይ 35 ርዕሰ-ብሔሮች፣ አራት ጠቅላይ ሚኒስትሮች፣ 11 የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች፣ 13 ቀዳማዊ እመቤቶችና 10 የዓለም አቀፍ ድርጅት ኃላፊዎች ይታዳማሉ ተብሏል።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር መለስ ዓለም በሰጡት ሳምንታዊ መግለጫ ከነገ ጀምሮ 36ኛው የአፍሪካ ሕብረት የመሪዎች ጉባዔ መካሄድ ይጀምራል፡፡
ቃል አቀባዩ በመግለጫቸው ጉባኤው የአፍሪካ ነፃ ንግድ ቀጣና ጉዳይ ላይ በስፋት እንደሚመክር ተናግረዋል።

በጉባኤው የፀጥታ ምክር ቤት ማሻሻያ እና የተለያዩ የሕግ ሰነዶች ይጸድቃሉ ተብሎ ይጠበቃል።
ቀጣዩ የአፍሪካ ሕብረት ፕሬዝዳንት ኮሞሮስ ከሴኔጋል ትረከባለች ብለዋል።

በአባቱ መረቀ
የካቲት 07 ቀን 2015 ዓ.ም

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ወቅታዊ አዳዲስ መረጃዎችና ፕሮግራሞችን ለማግኘት ከታች ያሉትን ገፆቻንን ይጎብኙ ቤተሰብ ይሁኑ ።

Telegram https://t.me/ethiofm107dot8
Twitter https://twitter.com/EthioFM
YouTube https://www.youtube.com/…/UCn4D20GPsAtNqN5bIC1BhFA/videos
Facebook https://www.facebook.com/onelovebroadcast
Website https://ethiofm107.com/
ያሎትን አስተያየት እና ጥያቄ በአጭር መልዕክት 6321 ላይ ይላኩልን።
ከኛ ጋር ስለሆናችሁ ከልብ እናመሰግናለን።

Source: Link to the Post

Leave a Reply