በአማኑኤል ይልቃል
የአዲስ አበባ ከተማ ትራንስፖርት ቢሮ በባለ ሶስት እና አራት እግር የ“ባጃጅ” ተሽከርካሪዎች ላይ የተጣለው እግድ ከነገ ቅዳሜ መጋቢት 8፤ 2015 ጀምሮ እንደሚነሳ አስታወቀ። የ”ባጃጅ” ተሽከርካሪዎች በየትኛውም ርቀት ከአምስት ብር በላይ ማስከፈል እንደማይችሉ ቢሮው ገልጿል።
የአዲስ አበባ ትራንስፖርት ቢሮ ይህንን ያስታወቀው የባለሶስት እና አራት እግር “ባጃጅ” ተሽከርካሪዎች አስመልክቶ ዛሬ መጋቢት 8፤ 2015 በሰጠው መግለጫ ነው። የቢሮው ኃላፊ አቶ ምትኩ አስማረ የባጃጅ ትራንስፖርት አገልግሎት የሚመራበት መመሪያ መዘጋጀቱን ለጋዜጠኞች ተናግረዋል።
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር “አገልግሎቱን ስርዓት ለማስያዝ” እያዘጋጀ ያለው “የአሰራር ማስተካከያ ተግባራዊ እስከሚሆን” በሚል “ባጃጆች” አገልግሎት እንዳይሰጡ ያገደው ባለፈው ሳምንት ሐሙስ የካቲት 30 ነበር። የከተማ አስተዳደሩ ከእግዱ መጣል በኋላ ባወጣው መግለጫ “የባጃጅ አሽከርካሪዎች ያልተገባ የዋጋ ጭማሪ በማድረግ እንዲሁም የተወሰኑት በወንጀል ድርጊቶች ላይ በመሰማራት የከተማችን ነዋሪ የቅሬታ ምንጭ ሆነዋል” ሲል ወቀሳ አቅርቦ ነበር። (ኢትዮጵያ ኢንሳይደር)
[በዚህ ዘገባ ላይ ተጨማሪ መረጃ ይታከልበታል]
The post በአዲስ አበባ በ“ባጃጅ” ተሽከርካሪዎች ላይ የተጣለው እግድ ከነገ ጀምሮ እንደሚነሳ የከተማው ትራንስፖርት ቢሮ አስታወቀ appeared first on Ethiopia Insider.
Source: Link to the Post