
በአዲስ አበባ በአማራ ልጆች ላይ የሚፈጸመው ስርዓታዊ የአፈና ወንጀል ተጠናክሮ እንደቀጠለ መሆኑ ተገለጸ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ሀምሌ 15/2015 ዓ/ም_አዲስ አበባ ኢትዮጵያ በአዲስ አበባ የካ ክ/ከተማ በአገዛዙ አካላት ሀምሌ 5/2015 በሌሊት አፈና የተፈጸመባቸው ብርሃኑ ንጉሴ አለሙ እና ሙላት ከፋለን በተመለከተ ከቤተሰብ የተነሳው ቅሬታ እና የአፋልጉኝ ጥሪ ማስተላለፋችን ይታወሳል። አሁንም በአማራ ልጆች ላይ የሚፈጸመው ስርዓታዊ የአፈና ወንጀል ተጠናክሮ እንደቀጠለ ስለመሆኑ ነው የሚሉት የአሚማ የመረጃ ምንጮች ዳንኤል አስረስ አሊጋዝ የተባለ ለፍቶ አዳሪ ታፍኖ ስለመወሰዱ ተገልጧል። ሀምሌ 4/2015 ከምሽቱ 2:30 መገናኛ አካባቢ ዲያስፖራ ሰፈር በጸጥታ አካላት ታፍኖ ስለመወሰዱ ተገልጧል። ቤተሰቦቹም ከቦታ ቦታ ቢንከራተቱም እስካሁን አድራሻውን ለማወቅ አልቻሉም፤ በከፍተኛ ጭንቀት ላይ ናቸው።
Source: Link to the Post