በአዲስ አበባ በአንድ ሰው መኖሪያ ቤት ከ170 በላይ የነዋሪነት መታወቂያ ወጥቶ ተገኘ።የከተማዋ ወሳኝ ኩነት ምዝገባ ኤጀንሲ ጉዳዩ ከሚመለከታቸው አጋር ተቋማት ጋር በአዲስ አበባ በመምከ…

በአዲስ አበባ በአንድ ሰው መኖሪያ ቤት ከ170 በላይ የነዋሪነት መታወቂያ ወጥቶ ተገኘ።

የከተማዋ ወሳኝ ኩነት ምዝገባ ኤጀንሲ ጉዳዩ ከሚመለከታቸው አጋር ተቋማት ጋር በአዲስ አበባ በመምከር ላይ ነው።

የአዲስ አበባ ወሳኝ ኩነትና ምዝገባ ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር ዶክተር ታከለ ነጫ ለኢትዮ ኤፍ ኤም እንዳሉት በከተማዋ አንዳንድ የኤጀንሲው ሰራተኞች ህገ ወጥ ተግባር ላይ መሳተፋቸውን ተናግረዋል።

በተጨማሪም በከተማዋ በአንድ ሰው መኖሪያ ቤት ከ170 በላይ የነዋሪነት መታወቂያ ወጥቷል ብለዋል።

ሌላ አንድ ሰው ደግሞ ከ50 ሰው በላይ የነዋሪነት መታወቂያ እንደወጣበትም ተናግረዋል።

ይህ የሆነው የቤት ባለቤቶች የስነ ምግባር ችግር ካለባቸው ጥቂት ከኤጀንሲው ሰራተኞች ጋር በመነጋገር እንደሆነ ተገልጿል።

በከተማዋ የሚገኙ አንዳንድ ነዋሪዎች በየመኖሪያ ቤታቸው ያሻቸውን መታወቂያ ያለ ገደብ በማሶጣት የነዋሪነት መታወቂያውን የገቢ ምንጭ ማድረጋቸውም ተሰምቷል።

የነዋሪነት መታወቂያውን ከ 2 ሺ ብር እስከ 7 ሺ ብር ድረስ በህገ ወጥ መንገድ ሲሰጡ የነበሩ ግለሰቦች መያዛቸውንም ተናግረዋል።

በመሆኑም ኤጀንሲው በቀጣይ በዚህ ህገወጥ ስራ ላይ በተሰማሩ ስነ ምግባር በጎደላቸው ሰራተኞች እና ባለንብረቶች ላይ እርምጃ እንደሚወስድ ዳይሬክተሩ ተናግረዋል።

በየውልሰው ገዝሙ
ሕዳር 1 ቀን 2013 ዓ.ም

Source: Link to the Post

Leave a Reply