በአዲስ አበባ በኢድ ሶላት ስነ ስርአት ላይ በተነሳ ረብሻ በ28 ተቋማት ላይ ጉዳት መድረሱ ተገለጸ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ሚያዝያ 24 ቀን 2014 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸ…

በአዲስ አበባ በኢድ ሶላት ስነ ስርአት ላይ በተነሳ ረብሻ በ28 ተቋማት ላይ ጉዳት መድረሱ ተገለጸ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ሚያዝያ 24 ቀን 2014 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ ሚያዝያ 24/2014 በአዲስ አበባ በኢድ ሶላት ስነ ስርአት ላይ በተነሳ ረብሻ በሰማዕታት ሃውልት፣ መስቀል አደባባይና የቂርቆስ ክፍለ ከተማ ህንጻን ጨምሮ በ28 ተቋማት ላይ ጉዳት መድረሱን የቂርቆስ ክፍለ ከተማ ሰላምና ፀጥታ ጽ/ቤት ገልጿል፡፡ ጽ/ቤቱ እንዳስታወቀው የረመዳን ፆም መጠናቀቁን ተከትሎ ህዝበ ሙስሊሙ በሰላማዊና ሀይማኖቱ በሚፈቅደው መንገድ በአዲስ አበባ ስታዲየም በዓሉን እያከበረና ለፈጣሪው ምስጋናውን እያቀረበ ባለበት ሰዓት ላይ ጥቂት ግለሰቦች ባስነሱት ረብሻ በንብረት ላይ ጉዳት ደርሷል ብሏል። ችግር ፈጣሪዎቹ ስታዲየም ውስጥ እና በዙሪያዋ ያሉ 28 ተቋማት ላይ ካደረሱት ጉዳት በተጨማሪ መስቀል አደባባይ የመኪና ማቆሚያ መግቢያና መውጫ መስታወቶች ላይ መጠነኛ ጉዳት አድርሰዋል፡፡ በሰማዕታት ሀውልትና አጠገቡ ያለው የመፅሀፍት መደብር እና ካፍቴሪያ እንዲሁም የቂርቆስ ክፍለ ከተማ ቢሮ ላይ ጉዳት መድረሱን የክፍለ ከተማው ሰላምና ፀጥታ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ታዬ ሽፈራው ተናግረዋል፡፡ እንደ አቶ ታዬ ማብራሪያም በከተማዋ የተለያዩ ስራዎችን እየሰራን ባለንበት በዚህ ወቅት ጥቂት ሰላማችን የሚያማቸው የውስጥ ጠላቶቻችን ከውጭዎቹ ታሪካዊ ጠላቶቻችን ጋር ያልተቀደሰ ጋብቻ በመፈፀም ሀገሪቱን ለማተራመስ እየሰሩ ነዉ ብለዋል፡፡ በተወሰኑ አካባቢዎች የተፈጠሩ አለመግባባቶችን መነሻ በማድረግ አብዛኛው አካባቢ ችግር ለመፍጠር መሞከር እንዲሁም ችግሩን ከወንድማማችነት እሴትና ከሀይማኖት አስተምህሮት ውጭ ለመፍታት መሞከር ውጤቱ የከፋ ይሆናል፤ ኢትዮጵያውያን ሁሌም የመቻቻል እሴታችን መሰረት ላይ መቆም ይገባናል ሲሉ አክለዋል ሲል ብስራት ራዲዮ ዘግቧል፡፡

Source: Link to the Post

Leave a Reply