በአዲስ አበባ ባለፉት ስድስት ወራት ውስጥ 31 ሰዎች በድንገተኛ አደጋ ህይወታቸው ማለፉ ተገለጸ።

የእሳትና የአደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን የኮሚኒኬሽን ባለሙያ አቶ ንጋቱ ማሞ ለኢትዮ ኤፍ ኤም እንደተናገሩት፣ ባለፉት ስድስት ወራት ውስጥ በአዲስ አበባና አካባቢዉ በአጋጠሙ 239 አደጋዎች ከ475 ሚሊየን በላይ ንብረት ሲወድም የአደጋ ጊዜ ሰራተኞች በአደረጉት ጥረት 7.8 ቢሊየን ብር የሚገመት ንብረት ማዳን ተችሏል ብለዋል።

ከደረሱት አደጋዎች መካከል 208 አደጋዎች በአዲስ አበባ ያጋጠሙ ሲሆን 33 አደጋዎች ደግሞ በኦሮሚያ ክልል ዉስጥ የተከሰቱ መሆናቸውን ተናግረዋል።

ከአደጋዎቹ ዉስጥ 150 የእሳት አደጋዎች ሲሆኑ 89 አደጋዎች ደግሞ ከእሳት ዉጪ ያጋጠሙ ናቸዉም ብለዋል።

የደረሱትን አደጋዎች ለመቆጣጠር በተደረገ ጥረት ቁጥራቸዉ 25 የሆኑ ሰዎችን ከአደጋዎች መታደግ መቻሉንም ተናግረዋል።

በሌላ በኩል 31 ሰዎች ከእሳት ዉጪ በአጋጠሙ ሌሎች ድንገተኛ አደጋዎች ህይወታቸዉ አልፎ የተገኙ ሰዎች አስከሬንን የኮሚሽኑ የአደጋ ጊዜ ሰራተኞች አንስተዉና አዉጥተዉ ለፖሊስ አስረክበዋል ነው ያሉት።

አደጋዎቹ ወንዝ ዉስጥ፣ተቆፍረዉ ክፍት በተተዉ ጉድጓዶች ዉስጥ፣በኤሌክትሪክና በመሳሰሉት አደጋዎች ህይወታቸዉ ያለፉ ናቸዉ ያሉ ሲሆን፣ ከነዚህ ዉስጥም ፖሊስ ምርመራ እያደረገባቸዉ ይገኛልም ተብሏል።

ከአደጋ ክስተት አንጻር አዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ 35 አደጋዎች የደረሱ ሲሆን ቦሌ ክፍለ-ከተማ 32 አደጋዎች ተከስቷል ብለዋል።

እንዲሁም በኮሌፌ ቀራኒዮ 30 አደጋ የተመዘገበ ሲሆን ዝቅተኛዉ አደጋ በልደታ ክፍለ ከተማ የደረሰ ሲሆን የደረሰው አደጋም 7 ሆኖ ተመዝግቧል ሲሉ ለኢትዮ ኤፍ ኤም ተናግረዋል።

በሔኖክ ወ/ገብርኤል

ጥር 21 ቀን 2016 ዓ.ም

Facebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Source: Link to the Post

Leave a Reply