በአዲስ አበባ ቦሌ መሰናዶ ትምህርት ቤት አካባቢ የደረሰው የእሳት አደጋ በቁጥጥር ስር ውሏል።

አደጋው የደረሰው ቦሌ ከኤድናሞል 22 ባለው መስመር ቦሌ መሰናዶ ትምህርት ቤት ፊት ለፊት ባለ አንድ የቻይና ኮንስትራክሽን ድርጅት መጋዘን ላይ ነበር።

የከተማዋ እሳት እና አደጋ ስጋት አመራር ኮሚሽን ሰራተኞች ወደ ቦታው ደርሰው አደጋውን ሙሉ በሙሉ መቆጣጠር ችለዋል።

የህንጻው ባለቤት ለኢትዮ ኤፍ ኤም እንዳሉት አደጋው ሆን ተብሎ እንዲፈጠር ስለመደረጉ ስጋት እንዳላቸው የተናገሩ ቢሆንም ፖሊስ ትክክለኛውን መንስኤ ለማወቅ በማጣራት ላይ ይገኛል።

በሔኖክ ወ/ገብርኤል
ሕዳር 7 ቀን 2013 ዓ.ም

Facebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Source: Link to the Post

Leave a Reply