በአዲስ አበባ ቦሌ ቡልቡላ ወረዳ 12 የሚኖሩ ከ20 በላይ የአማራ ልጆች በአድዋ ድል በዓል ዋዜማ ታስረዋል። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ የካቲት 22 ቀን 2015 ዓ/ም አ…

በአዲስ አበባ ቦሌ ቡልቡላ ወረዳ 12 የሚኖሩ ከ20 በላይ የአማራ ልጆች በአድዋ ድል በዓል ዋዜማ ታስረዋል። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ የካቲት 22 ቀን 2015 ዓ/ም አዲስ አበባ ሸዋ በአዲስ አበባ የአደባባይ በዓል በመጣ ቁጥር ዜጎችን በማንነታቸው እየለዩ ማሰር፣ ማዋከብ እና ማሳደድ የብልጽግና ስርዓት የተለመደ ስራው እያደረገው ስለመምጣቱ ነዋሪዎች ተናግረዋል። የእምዬ ምኒልክ፣ የአጼ ቴዎድሮስ እና የሌሎች ነገስታት ምስል እንዲሁም የእነ ብ/ጄኔራል አሳምነው ጽጌ እና የሌሎችም የአማራ ጀግኖች ምስል ያለበት ቲሸርት የለበሱ እና ይለብሳሉ የተባሉ የአማራ እና ሌሎች ኢትዮጵያዊያን እየተሳደዱ መታሰራቸው በእጅጉ የሚወገዝ የስርዓቱ አካሄድ መሆኑ ተመላክቷል። እንደአብነትም በቦሌ ቡልቡላ ክ/ከተማ ወረዳ 12 አለም ካፌ ገበያ ማዕከል ላይ የነበሩ ከ20 በላይ የአማራ ተወላጆች በአድዋ በዓል ዋዜማ በወረዳ 12 ፖሊስ ጣቢያ ታስረው ይገኛሉ። ከእነዚህም መካከል 8ቱ በድርድር ገንዘብ ከከፈሉ ወደ ፍ/ቤት ሳይወሰዱ እንደሚለቀቁ ተነግሯቸዋል ተብሏል። የካቲት 21/2015 ከምሽቱ 2 ሰዓት አካባቢ ጫላ የሚባል በየጊዜው በአማራዎች ላይ እየለዩ የግፍ እስር እና አፈና በተደጋጋሚ በመፈጸም ለተልዕኮ የተሰማራ የሲቪል ክትትል ስድስት ራሱን በመምጣት ምንም ጥፋት የሌለበትን አንዳርጌ አለህኝ የሚባል የኮንስትራክሽን ባለሙያን ጥይት በመተኮስ ጭምር ለማፈን ያደረገው ሙከራ አለመሳካቱ እና ወጣቱም ለጊዜው ከአካባቢው ሸሽቶ ስለማምለጡ ተገልጧል። የካቲት 22/2015 በአድዋ ድል ዋዜማ በግፍ ከታሰሩት ከ20 በላይ አማራዎች መካከል የሚከተሉት ይገኙበታለደ:_ 1. ሀይማኖት ይበልጣል፣ 2. አብነህ ዳኜ፣ 3. አሰሜ፣ 4. አይቸው፣ 5. እንመን፣ 6. መልካም፣ 7. ፍቅር፣ 8. ጌቱ፣ 9. ብናልፍ፣ 10. ይደግ ሀሳቤ፣ 11. ሀብታሙ ብዙአየሁ ይጠቀሳሉ።

Source: Link to the Post

Leave a Reply