You are currently viewing በአዲስ አበባ ት/ቤቶች በህጻናት ተማሪዎች ላይ የነገድ ፖለቲካን በሃይል ለመጫን የሚደረገዉ እንቅስቃሴ ሊቆም ይገባል ሲል ባልደራስ ገለፀ። የአማራ ሚዲያ ማእከል መስከረም 16 2015 ዓ/ም…

በአዲስ አበባ ት/ቤቶች በህጻናት ተማሪዎች ላይ የነገድ ፖለቲካን በሃይል ለመጫን የሚደረገዉ እንቅስቃሴ ሊቆም ይገባል ሲል ባልደራስ ገለፀ። የአማራ ሚዲያ ማእከል መስከረም 16 2015 ዓ/ም…

በአዲስ አበባ ት/ቤቶች በህጻናት ተማሪዎች ላይ የነገድ ፖለቲካን በሃይል ለመጫን የሚደረገዉ እንቅስቃሴ ሊቆም ይገባል ሲል ባልደራስ ገለፀ። የአማራ ሚዲያ ማእከል መስከረም 16 2015 ዓ/ም አዲስ አበባ ኢትዮጵያ ሙሉ መግለጫው እንደሚከተለው ይቀርባል። የመንግስት ስልጣንን በመጠቀም በትምህርት መጻህፍት ዉስጥ ታሪክን የሚያዛባ እና የፖለቲካ ፍላጎትን ባልተፈጸመ ትርክት ሽፍኖ በማስገባት አዲሱን ትዉልድ የሃሰት የታሪክ ትርክት ሰለባ እንዲሆን እና አትዮጵያዊ ማንነቱ በኦነጋዊ ማንነት እንዲተካ ለማድረግ የተጀመረዉ ጥረት ሊቆም ይገባዋል። ከዚህ አንጻር በአዲስ አበባ አንደኛ ደረጃ ትምህረት ቤቶች የኦሮምያ ክልል ባንዲራ እንዲተከል፣ የኦሮምያ ክልል መዝሙር እንዲዘመር፣ የአኖሌ ሃዉልት ፣ የግእዝ ፊደል ከግሪክ መጣ የሚል፣ በላይ ዘለቀን በተመለከተ ኦሮሞ ነዉ የሚሉ የሃሰት ትርክቶች በትምህርት ስረአቱ ውስጥ አንዲካተቱ መደረጋቸዉን ባልደራስ ለእዉነተኛ ዲሞክራሲ ፓርቲ በጽኑ ይቃወማል። የተለያየ ቅርጽና የቀለማት ስብጥር ይዞም ቢሆን፣ አርንጓዴ ቢጫ ቀይ የኢትዮጵያ ሰንደቅ የሃገረ መንግስቱ ባንዲራ በመሆን መታየት የጀመረዉ በ17 ኛዉ መቶ ክፍለዘመን መሆኑን የታሪክ መዛግብት ይዘክራሉ። በተለይም ደግሞ በአድዋ ጦርነት አማካይነት ኢትዮጵያ በአዉሮፓ ቅኝ አገዛዝ ላይ አኩሪ ድል ከተቀዳጀት በኋላ የአፍሪካ የነጻነት ትግል አረአያ እና አምበል ልትሆን እንደበቃች ይታወቃል። በዚህ ታሪካዊ ሃቅ መነሻነት ኢትዮጵያ የፓን አፍሪካ እንቅስቃሴ ማአከል እንድትሆን ስትደረግ ፣ መላ የአፍሪካ አገሮች ሃገራችን ኢትዮጵያ የለኮሰችዉን የነጻነት ችቦ አንገበዉ በመታገል ነጻነታችዉን ሲቀዳጁ፣ በርካታ የኣፍሪካ አገሮች በኢትዮጵያ ባንዲራ ዉስጥ ያሉ ሶስቱን አረንጓዴ ቢጫ ቀይ ቀለማት በመውረስ በተለያየ አቀማመጥ እና ቅርጽ ባንዲራቸዉ ዉስጥ ሊከቱ በቅተዋል። ይህም ማለት የኢትዮጵያ ባንዲራ የሃገራችን ህዝብ የነጻነት ተጋድሎ፣ የሃገራችን የአንድነት እና የሉአላዊነት አርማ ብቻ ሳይሆን፣ነጻ የአፍሪካ ህገሮችን ለነጻነት ትግል ያነሳሳ ሰንደቅ መሆኑን ያመለክታል። በዚህ አፍሪካዉያን በሚኮሩበት እንደ ሰንደቃችዉ አርገዉ በተቀበሉት አርማ ፣ መላ ኢትዮጵያዉያን ለዘመናት በኩራት ያነገቡትን ሰንደቅ ጽንፈኛ የነገድ ብሄረተኞች የሆኑት ህዉሃት፣ ኦነግ እና ኦህዴድ/ብልጽግና በኢትዮጵያ ፍርስራሽ ላይ የትግራይ እና የኦሮሞ ሪፐብሊኮችን ለመመስረት በማለም የሀገረ ኢትዮጵያ ሰንደቃአላማ ቦታ እንዳይኖረዉ እና በነዚህ ድርጀቶች ድርጅታዊ አርማዎች እንዲተካ እየተደረገ ያለዉን አካሄድ ፓርቲያችን ባልደራስ አበከሮ ይቃወማል። የኦሮምያ ክልላዊ መንግስት መዝሙርም በአዲስ አበባ ትምህርት ቤቶች ያለህዝብ ይሁንታ እና ፍቃድ ቋንቋዉን የማያዉቁ ህጻናት በግድ አንዲዘምሩት እየተደረገ ከመሆኑም በላይ በስረአተ ትምህርቱም ዉስጥ አንዲካተት ሁኗል። ከመዝሙሩ ስንኞች መካከል ኦሮምያ ኦሮምያ የታሪክ ባለቤት የኦሮሞዎች እምብርት የገዳ ስረአት መናገሻ የአመታት ጭቋናሽን በደም አጥበናል ባንዲራሽ ከፍ ብሏል በዉድ መስዋእትነት ተደስተናል ተደሰቺ ገዳ ስርአት ተመለሰልሽ የሚሉ የገኙበታል። ኦነግ/ኦህዴድ/ብልጽግና የመላ ኢትዮጵያ ነገዶች መናሕሪያ እና የሃገራዊ ዋና ከተማ በሆነችዉ አዲሰ አበባ ላይ የገዳ ስርአትን ለመትከል የጀመሩት አካሄድ ኢትዮጵያን ወደማፈራረስ የሚያመራ በመሆኑ፣ ይሄን የኦነግ/የኦህዴድ/ብልጽግና የፖለቲካ ፍላጎት የመንግስት ስልጣን ስለያዙ ብቻ በሌሎች የኢትዮጵያ ማህበረሰቦች ላይ በግድ ለመጫን የሚያደርጉት እንቅስቃሴ ቆመንለታል የሚሉትንም ህገ መንግስት ጭምር የሚቃረን በመሆኑ፣ ፓርቲያችን ባልደራስ እነዚህን ድርጊቶች ማዉገዝ ብቻ ሳይሆን እንዲቀለበሱም ይጠይቃል። በባልደራስ አመለካከት አኖሌ የተስፋየ ገብረአብ በ”ቡርቃ ዝምታ”የሴራ ፖለቲካ መጽሃፉ ያሰፈረዉ ፣ ወያኔ አገዛዙን ለማራዘም አማራና ኦሮሞን ለመከፋፈል ሲል በተስፋየ ገብረአብ እንዲጻፍ ካደረገዉ መጽሃፍ የተገኘ፣ አንድም የታሪክ መረጃ የማይገኝለት በሃሰት ትርክት ላይ የተመሰረተ የፈጠራ ዉጤት መሆኑን ያምናል። የግዕዝ ፊደልን በተመለከተ የስነ ጽሁፍ ተመራማሪዎች ( Epigraphists) እና የሥነልሳን/የቋንቋ ጠበብት ባካሄዱት ጥናት መሠረት የግእዝ ፊደል በጥንታዊ አረብያ ከመገኘቱ በፊት በአፌሪካ ቀንድ ሲገኝ ቢያንስ የሁለት ሺህ ዓመታት ቅድሚያ እንደነበረው ለማረጋገጥ ችለዋል፡፡ አሁን የምንጠቀምበት የግዕዝ ፊደል ምንጩ ከዚህ በፊት ሲታመን እንደነበረው ከአረብ ልሣነ ምድር ወደ ኢትዮጵያ እንደመጣ ይነገርለት ከነበረዉ የሳባ ቋንቋ ሳይሆን፣ ከአክሱም መንግሥት በፊት ከነበረው፣ ቋንቋውንና/ፊደሉን እንዲሁም መንግሥታዊ ሥልጣኔውን ለአክሱም መንግሥት ያወረሰው ጥንታዊው የደአማት መንግሥትና ሥልጣኔ ይጠቀምበት የነበረው ጽሐፍ እንደሆነ ፣ በዚህም በታወቁ የደች እና የሉክሰምበርግ የሥነቅርስና የስነቋንቋ ጠበብት የምርምር ግኝት መሰረት የግእዝ ፊደል ብቸኛዉ አፍሪካዊ ፊደል መሆኑ ተረጋግጧል፡፡ በላይ ዘለቀ ኦሮሞ ነዉ በማለት የኦሮሞ ብልጽግና በትምህርት መጻህፍት ዉስጥ እንዲካተት የተደረገዉም እንደዚሁ ከተስፋየ ገብረአብ “የቡርቃ ዝምታ” መጽሃፍ የተወሰደ ፍጹም ሃሰት የሆነ ዝባዝንኬ ነዉ። በዘመናዊ የኢትዮጵያ ታሪክ የኦሮሞ ማህበረሰብ በርካታ ለኢትዮጵያ ነጻነት እና አንድነት የተዋደቁ ጀግኖች እና አርበኞች እያሉት አላስፈላጊ የታሪክ እና የማንነት ሽምያ ውስጥ መግባቱ በእጀጉ የሚያስተዛዝብ ነዉ። ሃቁ በላይ ዘለቀ ላቀዉ አገኘሁ ከተባሉ የብቸና/ጎጃም ተዎላጅ አባቱ እና ጣይቱ አጽኔ ከተባሉ የአማራ ሳይንት ተዎላጅ እናቱ የተዎለደ አማራ ነዉ። የሴት አያቱ እንግዳየ ብሩ የተባሉ በብችና የለምጨን እና የሽበል በረንታ አማራ ናችዉ። የኦሮሞ ብልጽግና መንግስት የመንፈስ አባቱን የኦነግን የአማራ ጥላቻ በሃሰት ትርክት ከማስደገፍ አልፎ በወለጋ እና በሌሎች የኢትዮጵያ አካባቢዎች እየተካሄደ ያለዉን የአማራ ጭፍጨፋ ለማስቆም አለመፈለጉ ኦሮሞ ብልጽግና እና ኦነግ የአመለካከት መንትዮች መሆናቸዉን የሚያስረግጥ ሃቅ ነዉ። የባልደራስ ለዕውነተኛ ዲሞክራሲ ፓርቲ የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አዲስ አበባ /ኢትዮጵያ መስከረም 16/2015 ዓ.ም.

Source: Link to the Post

Leave a Reply