
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ውስጥ የተከሰተውን ችግር ተከትሎ ሰኞ ጥር 29/2015 ዓ.ም. ከተጀመረው የነነዌ ጾም ጋር ምዕመናን ጥቁር በመልበስ ምህላ እንዲያደርጉ ባዘዘችው መሠረት በተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች በርካታ ሰዎች ይህንን እየፈጸሙ ነው። ነገር ግን ይህንን ተግባራዊ ያደረጉ የእምነቱ ተከታዮች ላይ ወከባ እና እንግልት እንዲሁም በአንዳንድ አካባቢዎች አስር እንዳጋጠመ እየተነገረ ነው።
Source: Link to the Post