በአዲስ አበባ አቃቂ ቃሊቲ አዲሱ ማረሚያ ቤት ውስጥ ከፍተኛ የተኩስ ድምፅ እየተሰማ ነው ተባለ። (አሻራ፣ሚዲያ፣ጥር 16/2013 ዓ•ም ባህርዳር) በአዲስ አበባ ቃሊቲ አቃቂ አዲሱ ማረሚያ…

በአዲስ አበባ አቃቂ ቃሊቲ አዲሱ ማረሚያ ቤት ውስጥ ከፍተኛ የተኩስ ድምፅ እየተሰማ ነው ተባለ። (አሻራ፣ሚዲያ፣ጥር 16/2013 ዓ•ም ባህርዳር) በአዲስ አበባ ቃሊቲ አቃቂ አዲሱ ማረሚያ ቤት ውስጥ ከጠዋቱ 1:00ሰዓት ጀምሮ ከፍተኛ የተኩስ ድምፅ ይሰማ እንደነበር የአካባቢው ነዋሪዎች ለአሻራ ሚዲያ ገልፀዋል። በተኩስ ልውውጡ በርካታ ሰው ሳይሞት እንዳልቀረ የገለፁት የመረጃ ምንጫችን በግምት እስከ 2:30 ድረስ የተኩስ ድምፅ ይሰማ ነበርም ብለዋል።ማረሚያ ቤቱ ውስጥ ምን እንደተፈጠረ እርግጠኛ መሆን ባንችልም ጉዳዩ ከማረሚያ ቤቱ ፖሊሶች አቅም በላይ በመሆኑ የመከላከያ ሰራዊት መጥቶ ተኩሱን ማስቆሙን ማወቅ ችለናል ሲሉ ገልፀውልናል። አሻራ ሚዲያ በቦታው የተፈጠረውን ችግር እና የደረሰውን ጉዳት በተመለከተ ተጨማሪ መረጃዎችን እንዳገኘን ወደናንተ ይዘን እንቀርባለን። #አሻራ በዩዩቲዩብ ያገኙናልhttps://www.youtube.com/c/AMNMedia በቴሌግራም ያግኙን https://t.me/asharamedia24

Source: Link to the Post

Leave a Reply