በአዲስ አበባ አውራ ጎዳናዎች የሚታዩት የቢልቦርድ ማስታወቂያዎች የደረጃ ጥራት ችግር አለባቸው ተባለ፡፡ይህ ያለው የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የግንባታ ፍቃድና ቁጥጥር ባለስልጣን…

https://cdn4.telegram-cdn.org/file/Ul7Nip_aJCehmXaJiwTidHl7wEtVBfWLk3viD6bWtTtYatmeyyfjRK1MJyCDcR-9cAlroF4D5-t1l4pu6eCu8sCz0QicKMbe5X7sfZyeioFkN2K4lLupVvcrL-p5eqU4ouPXsRRl-HmmwkX0Vsyi74rcSOyKoCKKA7TpPcpHTOB13sunZvCgs3rzor9bo_bQzyW8iIV7aq2YZyvuJuGpfw9HIjK1xWM2JelHXasY8Ajv0TQiVmjknSeqJebX41MrBXFssZnGi5Lmn6ggo78I-y3v49CMBtxeFY4cbPKFySm8vLsqk_clCpovJ21WUdxYH8raVctp6Pvy5sBjFsP4Vg.jpg

በአዲስ አበባ አውራ ጎዳናዎች የሚታዩት የቢልቦርድ ማስታወቂያዎች የደረጃ ጥራት ችግር አለባቸው ተባለ፡፡

ይህ ያለው የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የግንባታ ፍቃድና ቁጥጥር ባለስልጣን ነው፡፡
ባለስልጣኑ ባለፉት ዘጠኝ ወራት ህገ ወጥ የውጭ ማስታወቂያዎችን ለመከላከል አደረኩት ባለው ጥናት ከ400 በላይ ቢልቦርዶች ደረጃቸውን የጠበቁ አይደሉም ሲል ለኢትዮ ኤፍኤም አስታውቋል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የግንባታ ፍቃድና ቁጥጥር ባለስልጣን የህዝብ ግንኙነትና የኮሙዪኒኬሽን ዳሬክቶሬት የሆኑት አቶ አረጋዊ ማሩ ለኢትዮ ኤፍኤም እንደተናገሩት ህጋዊ አሰራሩን ለመከተል ከ155 ሺህ በላይ ህገ ወጥ የውጭ ማስታወቂያዎች ላይ እርምጃ ወስደናል ብለውናል፡፡

በመዲናዋ ለውጭ ማስታወቂዎች ግልጋሎት የሚውሉ አካባቢዎች በተለያዩ ደረጃዎች ተለይዋል የተባለ ሲሆን ማስታወቂያዎችን ህጋዊ ማድረግ የሚያስችል ስታንዳርድ መዘጋጀቱንም ኢትዮ ኤፍኤም ከባለስልጣኑ ሰምቷል፡፡

የውጭ ማስታወቂያ ለሚያዘጋጁ ድርጅቶች ዳግም ምዝገባ በማድረግ የብቃት ማረጋገጫ ፈቃድ የሚሰጥም ይሆናል ነው የተባለው፡፡

ድርጅቶችም ደረጃቸውን የጠበቁ ማስታወቂያዎችን ብቻ ለማህበረሰቡ ተደራሽ እንዲያደርጉ ምልእክት ተላልፏል፡፡

ባለስልጣኑ ለከተማዋ ውበት የሚመጥኑ የውጭ ማስታወቂያዎች በብዛት ባለመኖራቸው በመዲናዋ ገጽታ ላይ አሉታዊ ተጽዕኖ እየፈጠረ እንደሆነም አስታውቋል፡፡

በመዲናዋ ህገ ወጥ የውጭ ማስታወቂያዎችን ለመከላከል ባለድርሻ አካላት በቅንጅት ሊሰሩ እንደሚገባም የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የግንባታ ፈቃድና ቁጥጥር ባለስልጣን ለኢትዮ ኤፍኤም አስታውቋል፡፡

በየዉልሰዉ ገዝሙ

ግንቦት 11 ቀን 2014 ዓ.ም

Source: Link to the Post

Leave a Reply