በአዲስ አበባ አዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ 2 ሰዎች በእሳት አደጋ ምክንያት ህይወታቸው ማለፉን ሰማን በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ወረዳ 10 ኬብሮን ካፌና ሬስቶራንት ውስጥ በተከሰተው የእሳት…

በአዲስ አበባ አዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ 2 ሰዎች በእሳት አደጋ ምክንያት ህይወታቸው ማለፉን ሰማን

በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ወረዳ 10 ኬብሮን ካፌና ሬስቶራንት ውስጥ በተከሰተው የእሳት አደጋ የ2 ሰዎች ሕይወት ማለፉን እንዲሁም 6 ሰዎች ላይ ጉዳት መድረሱን በአዲስ አበባ ከተማ የእሳት እና አደጋ ስጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን የአዲስ ከተማ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊ ም/ኮማንደር ሉሉ ሃይሉ ገልፀዋል።
ትላንት ምሽት 12:42 ሰዓት ላይ በተከሰተው የእሳት አደጋ መንስኤው በካፌና ሬስቶራንት ውስጥ የነበረው ሲሊንደር በመፈንዳቱ ምክንያት እንደሆነ ተገልጿል፡፡
እሳቱ ወደ ሌሎች እንዳይዛመት በእሳትና አደጋ ስጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን ሰራተኞች፣ ፖሊስና የአካባቢው ነዋሪዎች ባደረጉት ብርቱ ጥረት እሳቱ በቁጥጥር ስር መዋሉን ም/ኮማንደር ሉሉ ተናግረዋል ፡፡
መሰል አደጋዎች በተለይ የንግድ ተቋማት አካባቢ ሊከሰት ስለሚችል አስፈላጊውን ስልጠና በመስጠትና ለአደጋ አጋላጭ የሆኑትን ነገሮች በማስወገድ እንዲሁም ለአደጋ ጊዜ የሚያስፈልጉ ሁኔታዎችን ማመቻቸት ይገባል ሲል የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ነው የገለጸው ፡፡
ጥቅምት 08 ቀን ፣2014 ዓ.ም
ኢትዮ ኤፍ 107.8 የኢትዮጵያውያን

Source: Link to the Post

Leave a Reply