በአዲስ አበባ እናትና ልጅ በቤት መደርመስ አደጋ ህይወታቸው አለፈ፡፡መስከረም 25 ቀን 2015 ዓ ም በቂርቆስ ክፍለ ከተማ ወረዳ 3 ልዩ ቦታዉ ጎተራ ወንጌላዊት ህንጻ ጀርባ ሌሊት 10:1…

በአዲስ አበባ እናትና ልጅ በቤት መደርመስ አደጋ ህይወታቸው አለፈ፡፡

መስከረም 25 ቀን 2015 ዓ ም በቂርቆስ ክፍለ ከተማ ወረዳ 3 ልዩ ቦታዉ ጎተራ ወንጌላዊት ህንጻ ጀርባ ሌሊት 10:12 ሰዓት ላይ የመንገድ መደገፍያ የድጋፍ ግንብ በመኖሪያ ቤት ላይ ተደርምሶ በቤታቸዉ ተኝተዉ የነበሩ እድሜያቸዉ 35 እና የ7 ዓመት እናትና ልጅ ወዲያዉ ህይወታቸዉ አልፏል።

ድጋፍ ግንቡ መፍረሱን ተከትሎ የኮብልስቶን መንገዱም መሰረቱ ጭምር ተደርምሶ በቤቱ ላይ አርፎ አደጋዉን አባብሶታል።

የመኖሪያ ቤቱም የሚገኘዉ ከድጋፍ ግንቡና ከመንገዱ አምስት ሜትር ገደማ ዝቅ ብሎ የሚገኝ ነዉ።

የአደጋ ጊዜ ሰራተኞችና የአካባቢዉ ማህበረሰብ እንዲሁም የጸጥታ አባላት የሟቾችን አስከሬን ከፍርስራሽ ዉስጥ ማዉጣታቸዉንም የእሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን የህዝብ ግንኙነት ባለሙያዉ አቶ ንጋቱ ማሞ ነግረዉናል።

በቤቶች ዉስጥ የነበሩ አራት ሰዎች ከአደጋዉ አምልጠዉ እራሳቸዉን ማትረፍ ችለዋል።
በአደጋዉ ሶስት መኖሪያ ቤቶች ሙሉ በሙሉ መዉደማቸዉም ታዉቋል።

በየዉልሰዉ ገዝሙ
መስከረም 25 ቀን 2015 ዓ.ም

Source: Link to the Post

Leave a Reply