
በአደጋ ስጋት ደህንነት ደንብ 132/2014 ላይ ዛሬ የካቲት 21 ቀን 2015 በአዲስ አበባ ከሚገኙ የሆቴል ባለቤቶች ጋር ዉይይት ተካሂዷል።
ይህ የአደጋ ስጋት ደንብ ተቋማት አደጋን ተከላክለዉ ሰላማዊና ከአደጋ የተጠበቀ እንዲሆን የሚያስችላቸዉን መስፈርቶችን ያካተተና ደንቡን ተግባራዊ በማያደርጉት ላይ የተለያየ መጠን ያለዉ ቅጣትን የሚጥል ነዉ።
የአደጋ ስጋት ደንቡ በኮሚሽኑ ከፍተኛ አመራሮች በዝርዝር የቀረበ ሲሆን በደንቡ ላይ ቅሬታዎችን ጨምሮ የተለያዩ አስተያየትና ጥያቄዎች የቀርቡ ሲሆን ለቀረቡት ቅሬታዎችና ጥያቄዎች በኮሚሽኑ ከፍተኛ አመራሮች ምላሽና ማብራሪያ ተሰጥቷል።
በአዲሰ አበባ ከሚገኙ 180 ባለኮከብ ሆቴሎች ዉስጥ የአደጋ ስጋት ደህንነትን መስፈርትን ያሟሉ 10 ብቻ ናቸዉ በሌላ በኩልም ከ17 ሺህ 519 ተቋማት ዉስጥ ይህንኑ መስፈርት ያሟሉት 25 ብቻ መሆናቸውን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የእሳት እና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን የህዝብ ግንኙነት ባለሙያ አቶ ንጋቱ ማሞ ለኢትዮ ኤፍ ኤም ተናግረዋል።
በዚሁ የአደጋ ስጋት ደንብ ላይ የሚደረገዉ ዉይይት በቀጣይ ሳምንት ከኢንደስትሪ ባለቤቶች ጋር የሚደረግ መሆኑንም ጨምረው ገልጸዋል።
ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያዊያን
የካቲት 21 ቀን 2015 ዓ.ም
ለተጨማሪ መረጃዎች የቴሌግራምና የዩቲዩብ ቻናሎቻችንን ይቀላቀሉ!
Telegram https://t.me/ethiofm107dot8
YouTube https://www.youtube.com/@onelovebroadcast
ያሎትን አስተያየት እና ጥያቄ በአጭር መልዕክት 6321 ላይ ይላኩልን።
ከኛ ጋር ስለሆናችሁ ከልብ እናመሰግናለን።
Source: Link to the Post