በአዲስ አበባ ከተማ ልዩ ቦታው መገናኛ ተርሚናል አካባቢ በደረሰው የትራፊክ አደጋ የ5 ሰዎች ህይወት ማለፉን የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታወቀ፡፡
***
ዛሬ የካቲት 13 ቀን 2015 ዓ/ም ከምሽቱ 1፡15 ሠዓት አካባቢ በየካ ክ/ከተማ ወረዳ 9 ልዩ ቦታው መገናኛ ተርሚናል ላይ በደረሰው የትራፊክ አደጋ የ5 ሰዎች ህይወት ማለፉን የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታወቀ፡፡
አደጋው የተከሰተው ከመገናኛ ተርሚናል ጭኖ ሊወጣ የነበረ የሰሌዳ ቁጥሩ ኮድ 3_ A 36106 አ/አ የሆነ ሸገር ባስ የአደጋ ምክንያቱ ባልታወቀ ሁኔታ በአካባቢው በመንገድ ላይ የንግድ ሥራ ላይ በነበሩ 4 ሴቶችና 1 ወንድ ላይ ባደረሰው አደጋ ህይወታቸው ያለፈ ሲሆን ሌሎች በዚሁ አደጋ ጉዳት የደረሰባቸው ግለሰቦች ወደ የተለያዩ የህክምና መስጫዎች ተወስደዋል፡፡
የአደጋው ምክንያት በመጣራት ላይ የሚገኝ ሲሆን የአውቶብሱ አሽከርካሪም በቁጥጥር ስር መዋሉን የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታውቋል፡፡