በአዲስ አበባ ከተማ በአንዳንድ አካባቢዎች ለማሻሻያ ሥራ ሲባል የኃይል አቅርቦት እንደሚቋረጥ ተገለፀ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ   ህዳር 25 ቀን 2013 ዓ.ም         አዲስ አበባ ሸ…

በአዲስ አበባ ከተማ በአንዳንድ አካባቢዎች ለማሻሻያ ሥራ ሲባል የኃይል አቅርቦት እንደሚቋረጥ ተገለፀ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ህዳር 25 ቀን 2013 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸ…

በአዲስ አበባ ከተማ በአንዳንድ አካባቢዎች ለማሻሻያ ሥራ ሲባል የኃይል አቅርቦት እንደሚቋረጥ ተገለፀ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ህዳር 25 ቀን 2013 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ በአዲስ አበባ ከተማ በአንዳንድ አካባቢዎች ለማሻሻያ ሥራ ሲባል የኃይል አቅርቦት እንደሚቋረጥ በመግለፅ አስፈላጊው ቅድመ ጥንቃቄ እንዲደረግ የኤሌክትሪክ አገልግሎት አሳስቧል። በዚህም መሰረት ቅዳሜ ህዳር 26 ቀን 2013 ዓ.ም ከጠዋቱ 2፡00 እስከ ቀኑ 5፡00 ሰዓት ድረስ፣በኮተቤ ብረታ ብረት፣ በኮተቤ ኪዳነምህረት ቤተ-ክርስትያን፣ በአንቆርጫ እና አካባቢዎቻቸው አገልግሎት አይኖርም። በዚሁ ቀን ከጠዋቱ 2፡00 እስከ ቀኑ 8፡00 ሰዓት ድረስ፣በግብፅ ኤምባሲ፣ በስድስት ኪሎ ዩኒቨርሲቲ፣ በየካቲት ሆስፒታል፣ በቅድስተ ማርያም ቤተ-ክርስትያን ጀርባ፣ በእሪ በከንቱ፣ በፒያሳ፣ በቀይ ባህር ኮንደሚኒየም፣ በተፈሪ መኮንን ጀርባ፣ በአፍንጮ በር፣ በናይጄሪያ ኤምባሲ፣ በችሎት፣ በጉቶ ሜዳ እና አካባቢዎቻቸው የኤሌክትሪክ አገልግሎት ይቋረጣል። በተመሳሳይ ሰኞ እለት ህዳር 28 ቀን 2013 ዓ.ም ከጠዋቱ 2፡00 እስከ ቀኑ 6፡00 ሰዓት ድረስ፣በላምበረት፣ በመገናኛ፣ በየካ ሚካኤል፣ በሾላ ገበያ፣ በትምህርት ስርጭት፣ በእግዚአብሄር አብ ቤተ-ክርስትያን፣ በሜጋ እና አካባቢዎቻቸው የኤሌክትሪክ አገልግሎት ይቋረጣል። በተመሳሳይ ቀን ከጠዋቱ 1፡00 እስከ ቀኑ 9፡30 ሰዓት ድረስ፣በሃና ማርያም፣ በኃይሌ ጋርመንት፣ በቆጣሪ ኮንደሚኒየም፣ በኦሮሚያ ኮንደሚኒየም፣ በማንጎ ሰፈር፣ በወሰን ግሮሰሪ፣ በወንድይራድ ት/ቤት፣ በባድሜ ሰፈር እና አካባቢዎቻቸው፣በመካከለኛ የኤሌክትሪክ ተሸካሚ መስመር ላይ የማሻሻያ ሥራ ለማከናወን ሲባል የኃይል አቅርቦት የሚቋረጥ በመሆኑ፤ ክቡራን ደንበኞች ከወዲሁ አስፈላጊውን ጥንቃቄ እንድታደረጉ ሲል የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት አስታውቋል።

Source: Link to the Post

Leave a Reply