
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከነገ ጀምሮ የባጃጅ ትራንስፖርት አገልግሎት ተከለከለ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ የካቲት 29 ቀን 2015 ዓ/ም አዲስ አበባ ሸዋ ከየካቲት 30/2015 ጀምሮ በከተማዋ በየትኛውም አካባቢ ላልተወሰነ ጊዜ በሚል የባጃጅ አገልግሎት መከልከሉን የአዲስ አበባ ትራንስፖርት ቢሮ አስታውቋል። አሰራሩን ማሻሻል የሚለውን ቢሮው ለመከልከሉ እንደ ምክንያት የጠቀሰ ሲሆን የአገልግሎቱ አስፈላጊነትም በዝርዝር ተጠንቶ ውሳኔ እስኪያገኝ ድረስ ከየካቲት 30/2015ዓ.ም ጀምሮ በከተማዋ በየትኛውም አካባቢ ላልተወሰነ ጊዜ የባጃጅ ትራንስፖርት አገልግሎት የታገደ መሆኑን ቢሮው አሳውቋል ሲል አዲስ ሪፖርተር ዘግቧል። እገዳ ሳይጥሉ የማሻሻያ ስራውን እንዳይሰሩ ምን እንደከለከላቸው ግን የተገለጸ ነገር የለም።
Source: Link to the Post