በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የምክክር ምዕራፍ ሊጀመር ነው፡፡

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከነገ በስትያ ረቡዕ ግንቦት 21/2016 ዓ.ም የምክክር ምዕራፍ እንደሚጀመር የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን አስታውቋል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የምክክር ምዕራፍ ከነገ በስትያ ረቡዕ ግንቦት 21/2016 ዓ.ም ጀምሮ እስከ ግንቦት 27/2016 ዓ.ም እንደሚካሄድ ነው ኮሚሽኑ ዛሬ ለመገናኛ ብዙሃን በሰጠው መግለጫ ያስታወቀው፡፡

ከግንቦት 21 እስከ 27 2016 ዓ.ም የሚካሄደው መድረክ በአዲስ አበባ ከተማ ደረጃ የሚገኙ ባለድርሻ አካላት የአጀንዳ ግብአታቸውን የሚያዘጋጁበትና በሀገራዊ ጉባኤው የሚወክሏቸውን ተሳታፊዎች የሚመርጡበት እንደሆነ የኮሚሽኑ ምክትል ዋና ኮሚሽነር ሂሩት ገብረሥላሴ አስረድተዋል፡፡

በክልሎች እና ከተማ አስተዳደሮች የምክክር ምዕራፍ ላይ የሚሳተፉ ተወካዮች ከየኅብረተሰብ ክፍሉ መመረጣቸውን የገለጹት ኮሚሽነሯ፤ ኮሚሽኑ በምክክር ሂደቱ ትርጉም ያለው ተሳትፎን ለማረጋገጥ እየሠራ ይገኛል ብለዋል፡፡

ለሰባት ተከታታይ ቀናት በሚከናወነው መርሐግብር፤ ተሳታፊዎች በምክክርና በውይይት የአጀንዳ ሀሳቦችን እንደሚያመጡ እንዲሁም ለሀገራዊ ምክክር ጉባኤ ተሳታፊ የሚሆኑ ተወካዮቻቸውን እንደሚመርጡም በመግለጫው ተመላክቷል፡፡

በቀጣይነት ኮሚሽኑ ተመሳሳይ መርሐግብሮችን በድሬዳዋ ከተማ አስተዳደርና በክልሎች እንደሚከናወንም ተገልጧል፡፡

ኢትዮጵያዊያን የሚደገረውን የምክክር ሂደት ፋይዳ በመረዳት በንቃት እንዲትሳተፉ ኮሚሽኑ ጥሪ አቅርቧል፡፡

መረጃ የኮሚሽኑ የኮሚንኬሽን ክፍል ነው፡፡

ግንቦት 19 ቀን 2016 ዓ.ም

Facebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Source: Link to the Post

Leave a Reply