በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የትራፊክ ማኔጅመንት ኤጀንሲ የትራፊክ ቁጥጥር ባለሙያዎች የሚለብሱት የስራ ቦታ የደንብ ልብስን ይፋ አደረጓል።የኤጀንሲ የትራፊክ ቁጥጥር ባለሙያዎች…

https://cdn4.telegram-cdn.org/file/LCE669iFHfeiEkueoGaEig1p9PV_VGQ22mHF9249GMwQDl-60z5yAVdVke3BGs0FuQkjSlY-GCB_AdcK7NhPZ4NVaagOpULQ16f2ADJyCw7gueuiFY244skpf9kKcZSjQ2Q96BsqyJSgjj2miagxXE462NWSWVbLZwBVQ_dsE8_OFAO0r1imaFcL4vbaqyvXFDGvVju5yNZe3qOyvUnCdi_n5gsGAR9tx7DaHLDF2rqEg0QiRnq2RKSuFNLO_SazJ0VOsSNsi-uiDmRrrfhnajU_QMFywA5C5gqAZ9Wxw0AlLGMzk6ZcN4zT1oVfrKKwsh8L8BjcN_qhpxTLb5uiNA.jpg

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የትራፊክ ማኔጅመንት ኤጀንሲ የትራፊክ ቁጥጥር ባለሙያዎች የሚለብሱት የስራ ቦታ የደንብ ልብስን ይፋ አደረጓል።

የኤጀንሲ የትራፊክ ቁጥጥር ባለሙያዎች እስከ አሁን ድረስ ምንም ዓይነት የደምብ ልብስ ያልነበራቸው በመሆኑ እና የቁጥጥር ስራውን ለማጠናከር የሚያጠናከር እንደሚረዳ የትራፊክ ማኔጅመንት ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር አቶ ክበበው ሚደቅሳ ተናግረዋል፡፡

በተጨማሪም የደምብ ልብሱ ከዚህ በፊት አንፀባራቂ በመልበስ አሽከርካሪን አስቁሞ ተሽከርካሪውን ይዞ አስከመሰወር የደረሰን የሌብነትና የዘረፋ ተግባርን ለመከላከል እንደሚረዳ ተናግረዋል፡፡
ባለሙያዎቹ እስከ አሁን የደንብ ልብስ ስላልነበራቸው አንፀባራቂ ብቻ ለብሰው ሲሰሩ መቆየታቸው ከሌሎች ተቋማት ሰራተኞች እና የተለያዩ አካላት ጋር ተመሳሳይ በመሆኑ በተለይ አሽከርካሪዎች ሲያቀርቡት የነበረውን ቅሬተ የሚፈታም ጭምር ነው፡፡

በከተማዋ ላይ የትራፊክ ቁጥጥር ባለሙያዎች 920 የሚደርሱ መሆናቸው ተገልጿል

ሚያዝያ 08 ቀን 2014 ዓ.ም

ረድኤት ገበየሁ

Source: Link to the Post

Leave a Reply